የጣልያን ሴሪያ ሻምፒዮኑን አሳውቋል።
▪️የ2021/22 የውድድር ዘመን የጣልያን ሴሪያ ሻምፒዮን የሆነውን ክለብ እና ወደ ሴሪያ ቢ የወረደውን 3ኛ ክለብ ያላሳወቀው የጣልያን ሴሪያ በ38ኛ ሳምንቱ በርካታ ጨዋታዎችን አስተናግዷል።
▪️ሳሱሎ 0-3 ኤሲ ሚላን
17’32’⚽️⚽️ ጅሩድ
36’⚽️ ኬሲዬ
▪️ኤሲ ሚላን ወደ ስታዲዮ ማፔ አቅንቶ ሳሱሎን ገጥሞ 3-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ነጥቡንም 86 በማድረስ ከ2011 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቡዙ ውጣ ውረድ ፈተኖች በኋላ የስኩዴቶውን ዋንጫ ከፍ አድርገው ማንሳታቸውን አረጋግጠዋል።

▪️በቅርብ ርቀት ሲከተሏቸው የነበሩት የከተማ ተቀናቃኞቻቸው ኢንተርሚላን በሜዳቸው ሳንሲሮ ጁሴፔ ሜዛ ስቴዲየም ሳንፕዶሪያን አስተናግደው 3-0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል። ላለመውረድ በሚደረገው ጥረት ሳሌሪታና ከ ዩዲኔዜ እንዲሁም ቬኔዚያ ከ ካግላሪ ይገናኛሉ።
ሚካኤል ደጀኔ።
