ወጥ አቋም ማሳየት ያቃተው ባህርዳር ከተማ።

የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች በባህርዳር ስቴዲየም መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ረፋድ ላይ በተካሄደው መርሀ-ግብር።

▪️ባህር ዳር ከተማ 1-3 ሲዳማ ቡና
50’⚽️ዓሊ ሱለይማን    31’⚽️ጊት ጋትኩት    
                  43’⚽️ይገዙ ቦጋለ
                  59’⚽️ ሀብታሙ ገዛኸኝ

▪️ወጣ ገባ አቋም እያሳየ የሚገኘው ባህርዳር ከተማ በሜዳው ያደረገውን ጨዋታ በሲዳማ ቡና ተሸንፏል። ሲዳማ ቡና በበኩሉ አሰልጣኝ ገ/መድህን ሀይሌ ካሰናበተ በኋላ በተከታታይ ያስመዘገብ ሁለተኛ ድሉ ሆኖ ተመዝግቧል።

▪️ለሲዳማ ቡና 1 ግብ ያስቆጠረው ይገዙ ቦጋለ በውድድር ዘመኑ ያስቆጠራቸውን ግቦች 13 በማድረስ ከወዲሁ ኮኮቦ ጎል አግቢነቱን እየመራ ይገኛል።

▪️ውጤቱን ተከትሎም ሲዳማ ቡና ነጥቡን 40 በማድረስ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ

▪️ባህርዳር ከተማ በበኩሉ በ29 ነጥብ ባለበት 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

▪️ከጨዋታው በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️የባህርዳር ከተማው ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ 🗣 መጀመሪያዎቹ 20 ደቂቃዎች ላይ ያገኘናቸውን አጋጣሚዎች በሚገባ ተጠቅመን ቢሆን ኖሮ የጨዋታው ቅርፆ ይቀየር ነበር። ጎሎችን ከቆመ ኳስ እና ከመከላከል አደረጃጀት ክፍተቶቻችንጨበደንብ ያሳየ ነው። ለእረፍት ባሉን 20 ጠንክረን የምንሰራባቸው ጉዳዮች ይሆናሉ። ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

▪️የሲዳማ ቡና ምክትል አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ በበኩሉ  🗣 የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ የፈለግነውን ነገር አሳክተናል። 1 ጎል ያስቆጠረው ጊት ጋት ጉት ለብሄራዊ ቡድን መጠራቱ ምንም አይገርምም ልጁ ከዚ በላይ ማሳየት የሚችል አቅም አለው። ለብሄራዊ ቡድን መጠራቱ ደግሞ አቅሙን ይበልጥ እንዲያሳይ በር ከፋች ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️ሊጉ ለ20 ቀናት እረፍት ካደረገ በኋላ ሲመለስ ባህርዳር ከተማ ከ ቅ/ጊዮርጊስ ጋር እንዲሁም ሲዳማ ቡና ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.