የሚገባውን ሽኝት ያላገኘው ጋሬዝ ቤል።

▪️የስፔን ላሊጋ (የመጨረሻ) ሳምንት ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ሲጀምሩ ሎስ ብላንኮዎቹ ሪያል ቤቲስን በሳንቲያጎ ቤርናቦ አስተናግደዋል።በውድድር ዘመኑ ሪያል ማድሪድ በሜዳው ያደርገው የመጨረሻ መርሀ-ግብር ያለምንም ግብ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት የተጠናቀ ሲሆን ሻምፒዮን መሆኑን ከሳምንታት በፊት ላረጋገጠው ሪያል ማድሪድ የመርሀ-ግብር ማሟያ ጨዋታ ሲሆን ለሪያል ቤቲስ ግን በቀጣይ አመት የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊ መሆናቸውን ያረጋገጡቀት ሆኗል።

▪️በጨዋታው ላይ ዌልሳዊው ኢንተርናሽናል ጋሬዝ ቤል ሽኝት ይደረግለታል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ግን በቡድን ስብስብ ውስጥ መካተት አልቻለም።

▪️የ32 አመቱ ዌልሳዊ ኢንተርናሽናል እ.ኤ.አ በ2013 የአለማችን ውዱ ተጫዋች በመባል በ90 ሚሊዮን ፓውንድ ሳንቲያጎ ቤርናቦ ከደረሰ በኋላ ባደረጋቸው 256 ጨዋታዎች 106 ጎሎችን ሲያስቆጥር  67 ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። ከክሪስቲያኖ ሮናልዶ እና ካሪም ቤንዜማ ጋር በመሆን አስደናቂ የሶስትዮሽ ጥምረትም መፍጠር ችሎ ነበር።ከዚነዲን ዚዳን በላይ ብዙ ዋንጫወችን በክለቡ ያሳካ ፣ከዴቪድ ቤክሃም በላይ በክለቡ ብዙ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል የቻለ ፣ እንዲሁም ከሮናልዶ ልዊስ ናዛሪዮ ዴሊማ በላይ በክለቡ ብዙ ጎል ያስቆጠረ ተጫዋች ነው።

▪️ኮከቦቻቸውን በአግባቡ መሸኘት ልማድ የሌላቸው ሎስ ብላንኮዎቹ ለጋሬዝ ቤልም የሚገባውን ሽኝት ሳያደርጉለት ቀርተዋል። ቀጣይ ማረፊያው  እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እንደሚሆን የተለያዩ ምንጮች ከወዲሁ እየዘገቡ ይገኛሉ። የቀድሞ ክለቡ ቶተንሀም የዚህ ዌልሳዊ ኮኮብ ማረፊያ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.