ኢትዮጵያ ቡና ወደ ድል ተመልሷል።
▪️25ኛው ሳምንት የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በባህርዳር ስቴዲየም መካሄዳቸውን ቀጥለዋል። በ10 ሰአቱ መርሀ-ግብር
▪️ሀዋሳ ከተማ 1-3 ኢትዮጵያ ቡና
34’⚽️ ብሩክ በየነ 39’⚽️ አላዛር ሽመልስ
56’⚽️ዳግም ተፈራ (በራስ ላይ)
82’⚽️ አማኑኤል ዮሀንስ (ፍ.ቅ.ም)
▪️5ኛ እና 6ኛ ደረጃን ይዘው የተገናኙት ሁለቱ ቡድኖች 3 ነጥቡን የግላቸው ለማድረግ ብርቱ ፉክክር አድርገዋል።
▪️ሀዋሳ ከተማ በማጥቃት እና መከላከሉ ዘርፍ ላይ ቁልፍ ተጫዋቾቹን በጉዳት በማጣት ወደ ሜዳ የገባ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡናም በማጥቃት ዘርፉ ላይ አቡበከር ናስር እንዲሁም ዊልያም ሰለሞንን በ5 ቢጫ ካርድ ምክንያት ማሳለፍ አልቻሉም።
▪️ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 37 በማድረስ ለጊዜውም ቢሆን 4ኛ ደረጃን ከ ወላይታ ዲቻ መረከብ የቻለ ሲሆን ሀዋሳ ከተማ በበኩሉ በ36 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
▪️ሀዋሳ ከተማ ተከታታይ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።ባሳለፍነው ሳምንት በአርባምንጭ ሽንፈትን ማስተናገዳቸው የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በሀድያ ሆሳዕና ከተሸነፉ በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሱበት ውጤት ሆኗል።
▪️ከጨዋታው በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
▪️የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ 🗣 በስነ ልቦና ረገድ ጥሩ ውጤት ነው ብዬ እገምታለሁ። እንደ ቡድን ቅርፃችን ጥሩ ነበር። ዋናው ነገር ኳሶቻችን አለመቆራረጣቸው ነው። ያንን ካስጠበቅን ጥሩ እንቅስቃሴ እናደርጋለን ብለዋል።
▪️የሀዋሳ ከተማ አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ 🗣 ከእረፍት መልስ ምንም ጥሩ አልነበርንም። ቡድኑን በደንብ መፈተሽ ይኖርብናል። ብዙ መስተካከል ያሉባቸው ነገሮች ይኖራሉ። ለቀሪ ጨዋታዎች ከጉዳት የሚመለሱ ተጫዋቾች ስለሚኖሩ ጥሩ ውጤት ለማምጣት እና ደረጃችንን ለማስጠበቅ እንሞክራለን ብሏል።
ሚካኤል ደጀኔ።