የሉሲዎቹ እጣ ፈንታ በመልሱ ጨዋታ ይወሰናል።
▪️በህንድ አስተናጋጅነት ለ7ኛ ጊዜ በሚካሄደው የሴቶች ከ17 አመት በታች የአለም ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻ ዙር ላይ የደረሱት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከምዕራብ አፍሪካዋ ናይጄሪያ አቻቸው ጋር ዛሬ ቀን 10 ሰአት ላይ በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም ጨዋታቸውን አካሂዷል። አህጉራችንን አፍሪካ የሚወክሉ 3 የአፍሪካ ሀገራት ለመሆን በተደረገው ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ከመጠናቀቁ በፊት በ36ኛው ደቂቂ ላይ ኤስተር አጃካዬ ባስቆጠረችው ግብ ጨዋታው በናይጄሪያ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
▪️የኢትዮጵያ የሴቶች ከ 17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን የመልስ ጨዋታቸውን በናይጄሪያ ግንቦት 27 የሚያካሄዱ ሲሆን ውጤቱን የመቀልበሰ ግዴታ ውስጥ የገቡበትን ውጤት በሜዳቸው አስመዝግቧል። በመልሱም ጨዋታ 1 እና ከዛ በላይ ግብ አስቆጥረው ማሸነፍ ከቻሉ ወደ ህንድ ቲኬት መቁረጣቸውን ያረጋግጣሉ።
ሚካኤል ደጀኔ።