ፈረሰኞቹ ነጥብ ጥለዋል።

የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም በባህርዳር ኢንተርናሽናል ስቴዲየም መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።

▪️4 ሰአት ላይ በተካሄደው መርሀ-ግብር።

▪️ቅ/ጊዮርጊስ 0-0 ወላይታ ዲቻ

▪️የደረጃ ሰንጠረዡን የሚመራው እና 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቡድኖችን ያገኛነው ጨዋታ ምንም ግብ ሳያስተናግድ ተጠናቋል።

▪️ቅ/ ጊዮርጊስ የውድድር ዘመኑ 9ኛ አቻ ውጤት ሆኖም ተመዝግቧል።

▪️ወላይታ ዲቻ በበኩሉ የውድድር ዘመኑ 6ኛ አቻ ውጤት ነው ያስመዘገበው።

▪️የተሳኩ መልሶ ማጥቃቶች ላይ የተመሰረተ የጨዋታ ቅርፆ ይዘው ወደ ሜዳ የገቡት ወላይታ ዲቻዎች አንድ ነጥብ ከጨዋታው ይዘው መውጣት ችለዋል።

▪️ውጤቱን ተከትሎ ቅ/ጊዮርጊስ በ51 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡን ሲመራ ወላይታ ዲቻ በ36 ነጥብ ባለበት 3ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።

▪️ከጨዋታው በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️የቅ/ጊዮርጊሱ ምክትል አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ 🗣 ያሰብነውን ውጤት ይዘን አልወጣንም ፣ ከባድ ቡድን ነው የገጠምነው ግን የኛም ስህተቶች ነበሩብን አሁንም መጥፎ ሁኔታ ላይ አይደለም ያለነው ለቀጣይ ጨዋታዎች ውጤት ይዘን ለመውጣት እንሞክራለን ሲሉ

▪️የወላይታ ዲቻው አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማርያም በበኩላቸው 🗣 ተጋጣሚያችን አሳቢ ያደረገ አጨዋወት ይዘን ነበር የቀረብነው። ባሳለፍነው ሳምንት አዳማ ላይ 1 ጎል አግብተው መዝጋታቸው ይታወሳል ስለዚህ ጎል እንዳያስቆጥሩብን ሞክረናል እንደ ወላይታ ዲቻ ውጤቱ መጥፎ አይደለም። በውጤቱ ደስተኛ ነኝ ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️በቀጣይ ቅ/ጊዮርጊስ ከጅማ አባ ጅፋር እንዲሁም ወላይታ ዲቻ ከ ሲዳማ ቡና ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.