ለ100ኛ ጊዜ የተካሄደው የኮፓ ኢታሊያ የፍፃሜ ጨዋታ።
▪️ጁቬንትስ 2-4 ኢንተርሚላን
50’⚽️ ሳንድሮ 6’⚽️ ባሬላ
52’⚽️ ቭላሆቪች 80’⚽️ ቻላኖግሉ(ፍ/ምት)
99’⚽️ ፔርሲች( ፍ/ምት)
102’⚽️ ፔርሲች
▪️ለ100ኛ ጊዜ የተካሄደው የኮፓ ኢታሊያ ውድድር ጁቬንትስ ለ15 ጊዜ ለማንሳት ኢንተርሚላን ደግሞ ለ8ኛ ጊዜ ዋንጫውን የግላቸው ለማድረግ ብርቱ ፉክክር በስታዲዮ ኦሎምፒኮ ስቴዲየም አካሂደው መደበኛው 90 ደቂቃ 2 አቻ በሆነ ውጤት አጠናቀዋል።
▪️120 ደቂቃዎች የፈጀው የኮፓ ኢታሊያ የፍፃሜ ጨዋታ በተጨመሩት 30 ደቂቃዎች ኢንተርሚላን 2 ጎሎችን በማስቆጠር 4-2 በሆነ ውጤት ለ8ኛ ጊዜ የኮፓ ኢታሊያ አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
▪️ሮማ እና ላዚዮ በጋራ በሚጠቀሙት በስታዲዮ ኦሎምፒኮ ስቴዲየም በተካሄደው ጨዋታ የጁቬንትስ አሰልጣኝ ማርሲሚሊያኖ አሌግሪ ቀይ ካርድ ተመልክተዋል። ኢንተርሚላን በጨዋታው 2 የፍፁም ቅጣት ምቶችን አግኝቷል።
ሚካኤል ደጀኔ።