መድፉ የከሸፈበት አርሰናል ቀጣይ አመት ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ይሳተፍ ይሆን?

▪️በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተካሄደ ቀሪ መርሀ-ግብር በሰሜን ለንደን ደርቢ ቶተንሀምን ከአርሰናል ያገናኘ ነበር።

▪️22 ኛው ደቂቃ ላይ በአጨቃጫቂ መልኩ የጨዋታው ዳኛ ፖል ቲርኒ ነሰጡትን የፍፁም ቅጣት ምት ሀሪ ኬን ከመረብ በማዋሀድ ቡድኑን መሪ አደረገ።

▪️በ33ኛው ደቂቃ የቤን ዋይትን ጉዳት ተከትሎ እሱን በመተካት የመከላከሉን ሀላፊነት በመውሰድ ወደ ሜዳ የገባው ሌላው እንግሊዛዊ ሮብ ሆልዲንግ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። አርሰናል ወደ ጨዋታው እንዳይመለስ ያደረገ ከመሆኑም በላይ ቀሪውን 57 ደቂቃ በ10 ተጫዋች ለመጫወት ሚያስገድደውም ሆኗል። አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድኑን ከተረከበ በኋላ ቀይ ካርድ የተመለከተ 14ኛው ተጫዋች ያደገዋል።

▪️ከ4 ደቂቃ በኋላ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ ሀሪ ኬን በማስቆጠር የእለቱ ሁለተኛ በአጠቃላይ በሰሜን ለንደን ደርቢ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ደግሞ ወደ 13 ያሳደገች ግብ አስቆጠረ።

▪️ከእረፍት መልስ ያልተረጋጉት መድፈኞቹ ሁለተኛው አጋማሽ በተጀመረ 2 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የተገኘውን አጋጣሚ በአግባቡ በተጠቀመው ሶን ሁንግ ሚን አማካኝነት 3ኛ ግብ አስተናገዱ። ይህች ግብ በፕሪሚየር ሊጉ ወርቃማ ጫማ ለማግኘት በሚደረገው ፉክክር ላይ አስተዋጽኦ ያላት ናት። የውድድር ዘመኑ 21ኛ ግብ ሆናም ተመዝግባለች።

▪️ጨዋታውም 3-0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

የውድድር ዘመኑ ሊጠናቀቅ ሁለት ጨዋታዎች ሲቀሩት አርሰናል ወደ ሴንት ጄምስ ፓርክ አቅንቶ ኒውካስልን በሳምንቱ ደግሞ ኤቨርተንን በሜዳው ሲያስተናግድ ሁሉንም ጨዋታዎች የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ ለመውደቅ ይገደዳል። ቶተንሀም በበኩሉ በሜዳው ላለመውረድ እየታገለ ከሚገኘው በርንሌይ እና መውረዱን ካረጋገጠው ኖርዊች ሲቲ ጋር ጨዋታውን ያካሄዳል።

የሁለቱ ክለቦች የነጥብ ልዩነትም ወደ 1 ጠቧል። አርሰናል አሁንም በቀጣይ አመት የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ የመሆን እድሉ በእጁ ነው ግን የውድድር ዘመኑን ቀሪ ጨዋታዎች የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ ይገባል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.