የሉሲዎቹ ተተኪዎች ወደ መጨረሻው ምዕራፍ አልፈዋል። 

በመጪው መስከረም 29- ጥቅምት 20  በህንድ አስተናጋጅነት ለ8ኛ ጊዜ የሚከናወነው እና 16 ቡድኖችን አካቶ ለሚካሄደው የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ለማለፍ አፍሪካን የሚወክሉ 3 ሀገራት ለማወቅ በሚደረገው የማጣርያ ጨዋታ ላይ እየተካፈለ የሚገኘው  የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ ነው።

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድ ን3ኛ ዙር ላይ የደረሰ ሲሆን ከሁለት ሳምንት በፊት ጆሀንስበርግ ላይ የደቡብ አፍሪካ አቻውን 3-0 አሸንፎ  የተመለሰው ብሔራዊ ቡድናችን የመልሱን ጨዋታ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ  አበበ ቢቂላ ስቴዲየም አከናውኗል።

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከእረፍት በፊት በተቆጠረበት 1 ግብ ቢሸነፍም ደቡብ አፍሪካ ላይ 3 ለ 0 እሸንፎ በመመለሱ  3-1 በሆነ የድምር ውጤት ወደ 4ኛው እና የመጨረሻው ዙር ተቀላቅለዋል።

▪️በቀጣይ ግብፅን በደርሶ መልስ 6-0 አሸንፋ ቀጣይ ተጋጣሚዋን እየጠበቀች ከምትገኘው ከናይጄሪያ 17አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.