ሮማን አብራሞቪች ታግደዋል
▪️ዘ ኢንዲፔንዳንት ዘገባ ከሆነ በቦሪስ ጆንሰን የሚመራው የእንግሊዝ መንግስት የቼልሲውን ራሺያዊ ባለሀብት ሮማን አብራሞቪች ራሺያ በ ዩክሬን የፈፀመችውን ወታደራዊ ጥቃት በመቃወም በእንግሊዝ ያላቸውን ንብረትን እንዳያንቀሳቅሱ ወስኗል።
▪️የእንግሊዝ መንግስት ራሺያዊው ቢሊየነርን ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ባላቸው ቅርበት ምክንያት ከሁሉም ቦታዎች ማገዱን ተከትሎ ቼልሲን ለመሸጥ ሮማን አብራሞቪች የሚያደርጉት ጥረት የመሳካቱ እድል አነስተኛ መሆኑ ተገልጿል።
▪️ቼልሲ ከዛሬ ጀምሮ ያሉት የትጥቅ መሸጫዎች እንዲሁም ሱቆች አገልግሎት እንዳይሰጡ የተደረገ ሲሆን ከክለቡ የአመት ቲኬት ባለቤቶች ውጪ ደጋፊዎች ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ መግባት እንደማይችሉ ተገልጿል።ክለቡ በተጨማሪ ገንዘብ ምንጭ እንዳያገኝ የተደረገ ድርጊት ነው። ሮማን አብራሞቪችም የምዕራብ ለንደኑን ክለብ በመሸጥ ገቢ ማግኘት እንዳይችሉ ታግደዋል።
ሚካኤል ደጀኔ።