ታዋቂው ጋዜጠኛ ታሪኬ ቀጭኔ  አርፏል።

የእግር ኳስን በክለብ ደረጃ ለምድር ጦር፣  ለመብራት ሀይል እና ለምድር ባቡር  ክለቦች ተጫውቶ አሳልፏል። በኢትዮጵያ  የተስፋ ቡድን ውስጥም አልፏል።
በእግር ኳስ ችሎታው ድንቅ የነበረው ይኸው ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ ታሪኬ ቀጭኔ  ባጋጠመው የስኳር ህመም ምክንያት በቅርቡ  ሁለት አይኖቹን ያጣ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከዚህ አለም በሞት ተለይቶናል።

▪️ታዋቂው  የስፖርት  ጋዜጠኛ ታሪኬ ቀጭኔ  በስራ ህይወት ቆይታው በካምቦሎጆ ጋዜጣ ላይ ለረጅም ጊዜያት  ያህል ሰርቷል። የኢትዮጵያ  እግር ኳስ ገፅታም ምን እንደሚመስል የስፖርት መፅሔትን ከማዘጋጀት በተጨማሪ  የፎቶ ኢግዚቢሽን ማዘጋጀቱም ይታወሳል።

▪️ጋዜጠኛ ታሪኬ ቀጭኔ በስራ ቆይታው ከካምቦሎጆ  ጋዜጣ ውጪ ልሳነ ጊዮርጊስ በሌሎችም ላይ ተሳትፎን ያደርግ የነበረ ሲሆን ህመሙ እስከፀናበት ጊዜም ድረስ በቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ የህዝብ ግንኙነት ሆኖ ሰርቷል።

▪️በቂርቆስ አካባቢ ተወልዶ ያደገው ታዋቂው ጋዜጠኛ ታሪኬ ቀጭኔ በህይወት  ዘመን ቆይታው  ከሰዎች ጋር በመልካም ግንኙነቱ የሚታወቅ እና ሰው አክባሪም ነው። የቀብር ስነ-ስርዓቱም ነገ በ6 ሰዓት በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።
በታዋቂው ጋዜጠኛ ታሪኬ ቀጭኔ ሞት ኢትዮጵያን ስፖርት ዶት ኮም የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ፈጣሪ ነፍሱን ከደጋጎቹ  ጎን እንዲያሳርፋትና ለቤተሰቦቹም መፅናናትን ይመኛል።

ፈለቀ ደምሴ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.