ናራዙሪዎቹ በአሳዛኝ መልኩ ከሻምፒዮንስ ሊግ ውጪ ሆነዋል።
የሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ከ3 ሳምንት በፊት በሳንሲሮ ጁሴፔሜዛ በመጨረሻዎቹ 15 ደቂቃዎች በሮቤርቶ ፊርሚንሆ እና ሞሀመድ ሳላህ ግቦች ታግዘው 2-0 አሸንፈው መመለሳቸው ይታወሳል።
የመልስ ጨዋታውን በሜዳቸው አንፊልድ ኢንተርሚላንን የጋበዙት ቀያዮቹ የመጀመሪያውጨአጋማሽ ብዙም ማጥቃት ላይ ትኩረት ያላደረገ ግን ኳስ በመያዝ ላይ ተጠምደው አምሽተዋል። ከእረፍት መልስ ብዙም ለውጥ ያልተመለከትንበት ሲሆን ኢንተርሚላን ከፊት ያሰለፋቸው አጥቂዎቹ ላውታሮ ማርቲኔዝ እና የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ እና የአርሰናል ተጫዋች የነበረው አሌክሲስ ሳንቼዝ የቀያዮቹን የተከላካይ አጥር ሰብረው መግባት ተስኗቸው ነበር። ግን በ 66ኛው ደቂቃ ላይ ላውታሮ ማርቲኔዝ ከሳጥን ውጪ 16 ከ 50 ላይ የጠቀለለው ኳስ አሊሰን ቤከር መረብ ላይ አርፏል።
ይህች ግብ ከአተቆጠረች ከ3 ደቂቃ በኋላ ቺሊያዊው አሌክሲስ ሳንቼዝ ፋቢንሆ ላይ በሰራው ጥፋት በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ናራዙሪዎቹ ቀሪውን 25 ደቂቃ በ10 ተጫዋች ለመጫወት ተገደዋል። ከዚ ወዲህ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ አፈግፍገው የተጫወቱት ኢንተርሚላኖች 1-0 በሆነ ውጤት ቢያሸንፉም በድምር ውጤት 2-1 በሆነ ውጤት ተሸንፈው ከውድድሩ በአሳዛኝ መልኩ ቢሰናበቱም የሊቨርፑል የ12 ጨዋታዎች በሜዳቸው ያለመሸነፍ ጉዞ በምሽቱ ጨዋታ መግታት ችለዋል።
ሚካኤል ደጀኔ።