የ2014 ከ20 አመት በታች ታዳጊ ወጣቶች  የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርአት ተካሂዷል።

▪️ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የእጣ አወጣት ስነ-ስርአት ዛሬ በጁፒተር ሆቴል ተካሂዷል። ዘንድሮ ወድድሩ በሁለት ምድብ ተከፍሎ በጎንደር እና በአሰላ ይካሄዳል።በጎንደር ከተማን የመረጥነው እና ውድድሩን እንድታስተናግድ ያደረግነው ሀገራችን ሰላም መሆኗን ለማረጋገጥ ነው ተብሏል ውድድሩ የካቲት 12 ይጀምራል። የ2013 ከ20 አመት በታች አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል በሪፖርቱ  የኤም አር አይ (MRI) በ2013 ትልቅ እንቅፋት እንደነበር። ጳውሎስ ሆስፒታል ማሽኑ ተበላሽቶ ስለነበር ሪፖርት አደራረግ ላይ ክፍተቶች ነበሩ። በ2013 ከ20 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ መድህን እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና በቅደም ተከተል ከ1 እስከ 3 ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ ችግሮች የሚታዩ መሆኑን ማለትም ጊዜ መግደል እንዲሁም የተጎዱ እያስመሰሉ ሜዳ ላይ መተኛት ታዳጊዎች ፣ ተተኪዎች እንደመሆናቸው መጠን ራሳቸውን ሊያሻሽሉ ፣ ብቃታቸውን ማዳበር ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው በመጠቆም ሀድያ ሆሳዕና በዚህ ረገድ ጥሩ በመንቀሳቀሱ የአምና ስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ ተበርክቶለታል። ከ20 አመት በታች በቴክኒክ ዳይሬክቶሬት ዳታ መሰብሰብ እንዳለበት ተነስቷል።

▪️የ2014 ደንብ  ከ 2013 የተሻሉ ነገሮችን አካቷል። ለምሳሌ ተጠባባቂ ወንበር ታዳጊዎች እንደመሆናቸው መጠን 12 ተጫዋቾች ተጠባባቂ ወንበር ላይ መቀመጥ ይችላሉ። 5 ተጫዋቾች ቅያሪ ማድረግም ሚቻል ሲሆን ማጠቃለያ ጨዋታዎች አይኖሩም። የምድብ 1 እና ምድብ 2 አሸናፊዎች ለምርጥ አንደኝነት ይጫወታሉ። ሁሉም ተጫዋቾች ኮቪድ ሪፖርት ይዘው መምጣት አለባቸው ከ10 ተጫዋች በላይ በኮቪድ የተጠቃበት ቡድን ውድድር ማድረግ አይችልም።በደንቡ ላይ ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎች ከቡድን መሪዎች እንዲሁም አሰልጣኞች የተነሱ ሲሆን በቴክኒክ ክፍሉ በአቶ ቴዎድሮስ እንዲሁም በሊጉ አስተዳደር ክፍል ወ/ሮ መሰረት መልስ ተሰጥቶባቸዋል። ከተነሱ ሀሳቦች መሀከል ሁሉም ቡድኖች ተተኪ ማፍራት ላይ እንዲሰራ እና ለዚህም ተጫዋቾቻቸውን እንዲመዘግቡ  ሜዳ ላይ ያሳዩትን እንቅስቃሴ (heat map) ፣ ብቃታቸው ምንድን ነው ሚለውን እንዲመዘግቡ የቴክኒክ ክፍሉ ቅጽ አዘጋጅቷል። ይህንን ቅጽ በየጊዜው በመሙላት የተጫዋቾቹን ብቃት ገምግመው ሚመዘግቡበት መንገድ ነው። ይህም ተተኪዎችን እንዲፈሩ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ያደርጋል ሲሉ የቴክኒክ ክፍሉ አቶ እንዳለየሱስ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ደንቡም በሙሉ ድምፅ ጸድቋል። 19 ቡድኖች በሁለት ምድብ ተከፍለው የሚጫወቱ ይሆናል።የእጣ ማውጣት ስነ ስርአቱ ተካሂዷል።

▪️ምድብ 1
ሀላባ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ሰበታ ከተማ ፣ ሀድያ ሆሳዕና ፣ ባህርዳር ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ወላይታ ዲቻ ፣ አርባምንጭ ፣ አዳማ ከተማ ፣ ኢትዮ ኤሌትሪክ

▪️ምድብ 2
አዲስአበባ ከተማ ፣ወላይታ ዞን ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ድሬዳዋ ከተማ ፣ ቅ/ጊዮርጊስ ፣መከላከያ ፣ ኢትዮጵያ መድህን ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ፋሲል ከነማ ተደልድለዋል።

ምድብ 1 የተደለደሉ ቡድኖች ጎንደር ውድድራቸውን ሲያካሄዱ ምድብ 2 የተደለደሉት ቡድኖች ወደ አሰላ የሚያቀኑ ይሆናል።

▪️የመጀመሪያው ሳምንት ጨዋታዎች በሁለቱም ቦታዎች የካቲት 12 የሚካሄዱ ሲሆን
▪️ወላይታ ዞን ከ ፋሲል ከነማ
▪️ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና
▪️ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድህን
▪️ቅ/ጊዮርጊስ ከ መከላከያ የሚገናኙ ይሆናል።

ፈለቀ ደምሴ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.