የፍጻሜው ትንቅንቅ።
33ኛው የቶታል ኤነርጂስ የአፍሪካ ዋንጫ ለአንድ ወር ተካሂዶ ለፍፃሜ የደረሱ ሁለት ቡድኖችን አፋልሞ ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል። የቴራንጋ አንበሶቹን ሴኔጋሎችን ከ ፈርኦኖቹ ግብጽ ጋር አፋጧል። እነዚህ ሁለት ቡድኖች ባለፉት ግንኙነታቸው ግብጽ የበላይነት ትወስዳለች። 6ጊዜ ስታሸንፍ ሴኔጋል 4 ጊዜ አሸንፋለች። ሁለቱም ቡድኖች ውስጥ በሊቨርፑል ቤት ስኬትን የተጎናጩ የሚጫወቱት ሳድዮ ማኔ እና ሞሀመድ ሳላህ የቡድን አጋሮች ቢሆኑም ዛሬ ሀገራቸውን ወክለው በተቃራኒ ተፋጠዋል። ሁለቱም ተጫዋቾች ለሁለተኛ ጊዜ ለፍፃሜው የደረሱ ሲሆን ሳድዮ ማኔ ከሁለት አመት በፊት በ2019 የተዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለፍፃሜ ደርሰው በአልጄሪያ ዋንጫውን መነጠቃቸው ይታወሳል ዘንድሮም ለዋንጫው በመድረስ ጠንካራ ብሄራዊ ቡድን እንደሆኑ አሳይተዋል። ግብጽም ለመጨረሻ ጊዜ ለዋንጫ የደረሰችው በ2017 ሲሆን ዋንጫውን በካሜሩን መነጠቃቸው ይታወሳል። ስለዚህ ሁለቱም ቡድኖች ዋንጫውን ከፍ አድርገው ለማንሳት ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርጉ በሁሉም ስፖርት ቤተሰቦች ሚጠበቅ ነገር ነው።ኦሌምቤ ስታዲየም ይህን ጨዋታ ያስተናገደ ስቴዲየም ነው።
የጨዋታው ከተጀመረ ገና በ7ኛው ደቂቃ ላይ የግብጹ ተከላካይ አብዴልሞኔም የሴኔጋሉ ተከላካይ ሶሊዮ ሲስ ላይ የሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ሳዲዮ ማኔ ሳይጠቀምበት ቀርቷል። ሳዲዮ ማኔ የግብጹ ግብጠባቂ እና ሞሀመድ ሳላህ በሚነጋገሩበት ሰአት ወደ እነሱ በማቅናት “ወደ ጎልህ ግባ ቅጣቱን ልመታ ነው” እንዳለ በጥቆማው መረዳት ይቻላል። የግብጹ ግብ ጠባቂ አብዱጋባል በትክክል ቦታውን በመገመት ኳሱን አውጥቷል።

ከዚ በኋላ ግብጽ በመሀመድ ሳላህ አማካኝነት አስደንጋጭ ሙከራ ማድረግ ቢችሉም የቼልሲው ግብ ጠባቂ ኤድዋርድ ሜንዲ ግቡን ሳያስደፍል ሁለቱም ቡድኖች ለእረፍት ወተዋል።ከእረፍት መልስ በአንፃራዊነት ሴኔጋሎች በሙከራ ረገድ ደከም ብለው ታይተዋል በአንፃሩ የግብጽ ብሄራዊ ቡድን ተቀይሮ በገባው አጥቂው ሀምዲ አማካኝነት ኢላማውን ያልጠበቀ ሙከራ ከማድረግ ባለፈ ያን ያህል ግብጠባቂው ሜንዲን የፈተነ ሙከራ አላደረጉም።መደበኛው 90 ደቂቃ በአቻ ውጤት መጠናቀቁን የምሽቱ አልቢትር ደቡብ አፍሪካዊው ቪክተር ጎሜዝ በፊሽካቸው አብስረዋል።ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ ሁለቱም ቡድኖች አምርተዋል። ግብጽ በ10 ቀናት ልዩነት 120 ደቂቃዎች መጫወት ችለዋል ግን ምንም የድካም ስሜት አልታየባቸውም ለዛማሌክ በሚጫወተው ዚዞ አማካኝነት ጥሩ ሙከራ ስራ ፈቶ በነበረው ሜንዲ ላይ መሞከር ችለው ነበር በአንፃሩ ሴኔጋሎች በዲዬንግ ጥሩ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ መሞከር ችለዋል። ተጨማሪ ደቂቃው በዚ አይነት ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን ለ2 ሰአት የቆየው ጨዋታ በሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስተናግድ ወደ መለያምት አምርተዋል።
በመለያ ምቱ በግብጽ በኩል ተከላካዩ አብዱልሞኔም እንዲሁም መሀመድ ላስሄን ሲያመክኑ
በሴኔጋል በኩል ቦኑ ሳር የመለያ ምቱን አምክነዋል።

በዚህም መሰረት ሴኔጋል 4-2 በማሸነፍ
ሴኔጋል 15ኛው አዲስ ሀገር በመሆን በታሪኳ ከ 64 አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ከፍ አድርጋ መሳም ችላለች።

የጨዋታው ኮኮብ የግብጹ ግብ ጠባቂ አብዱል ጀመል አሊ መሆን ችሏል።
▪️የአፍሪካ ዋንጫ የውድድሩ ምርጥ ግብ ጠባቂ በመባል የቼልሲው ኤዱዋርድ ሜንዲ ተመርጧል።

▪️የውድድሩ ኮኮብ ግብ አስቆጣሪ የካሜሩኑ ቪንሰንት አቡበከር ሆኗል።

▪️የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች የሊቨርፑሉ ሳድዮ ማኔ ተብሎ ተመርጧል።

ሚካኤል ደጀኔ።
