የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ወደ አለም ዋንጫው ያልፉ ይሆን?
▪️ዘንድሮ በኮስታሪካ አዘጋጅነት ለ 10ኛ ጊዜ የሚካሄደው ከ20 አመት በታች የሴቶች የአለም ዋንጫ የፊታችን ነሀሴ 2 እስከ 20 ይካሄዳል። አምና በኮቪድ ምክንያት መከናወን ያልቻለው ይህ ውድድር ዘንድሮ በኮስታሪካ አዘጋጅነት ይካሄዳል።ኮስታሪካ ከዚህ በፊት ከ17 አመት በታች የአለም ዋንጫ ማዘጋጀቷ ይታወሳል። 16 ቡድኖች ሚካፈሉበት ይህ የአለም ዋንጫ 32 ጨዋታውችም ይስተናግዳል። የሴቶች እግርኳስ እንዲበረታታ እና እንዲያድግ የራሱን ሚና ሚጫወተው ይህ መድረክ ላይም የኢትዮጵያ ከ 20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ለመካፈል በ4ኛው ዙር ከታንዛኒያ አቻው ጋር የደርሶ-መልስ ጨዋታ ይጠብቀዋል። ይህ ጨዋታን ማሸነፍ ከቻለ ከጋና እና ከዩጋንዳ አሸናፊ ጋር ምትገናኝ ይሆናል። የመጀመሪያ ጨዋታውን የፊታችን እሁድ ጥር 15 በታንዛኒያ በኡንጉጃ ከተማ አማኒ ስታዲየም ሚያከናውኑ ይሆናል።
የመልስ ጨዋታውን ከ ሁለት ሳምንት በኋላ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚያከናውን ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ለዚህም ጨዋታ ለተከታታይ 10 ቀናት ልምምድ ሲያደርጉ የቆየ ሲሆን ዛሬ የመጨረሻ ልምምዳቸውን በቅዱስ ጊዮርጊስ ሜዳ ሰርተዋል።
ይህንን ጨዋታ አስመልክቶ እና ስለ ቡድኑ ዝግጅት ወሎ ሰፈር በሚገኘው በእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ፆህፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።
ፈለቀ ደምሴ።