ሰለሞን ባረጋ በሊዬቪን የአለም ሪከርድን ያሻሽል ይሆን?

▪️በፈረንሳዩ ከተማ ሊዬቪን የሚካሄደው የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን የካቲት 9 የሚካሄድ ሲሆን አዘጋጆቹ እንደገለፁት ከሆነ አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ 3000 ሜትር ሪከርድ ጭምር ለማሻሻል እንደሚሮጥ አስታውቋል።

▪️የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የብር ሜዳሊስቱ ሰለሞን ባረጋ አምና በዚሁ በሊዬቪን ከተማ 7:26:10 በመግባት 2ኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቆ ነበር። ሌላው የሀገሩ ልጅ ጌትነት ዋሌ 7:24:98 በመግባት 1ኛ ሆኖ ነበር ውድድሩን ያጠናቀቀው። ኬንያዊው ዳንኤል ኮማን ይህንን ርቀት 7:24:90 በማጠናቀቅ የሪከርዱ ባለቤት እንደሆነ ይታወቃል።

▪️የ 21 አመቱ ሰለሞን ባረጋ በፖላንዷ ቶሩን ከተማ በ 1500 ሜትር የግሉን ምርጥ ሰአት 3:32:97 በማስመዝገብ 1ኛ ሆኖ ውድድሩን ማጠናቀቁ ከዛም በ ቶኪዮ ኦሎምፒክ በ10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አጥልቆ ሀገሩን በትልቅ መድረክም ማስጠራት ችሏል።

▪️በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በሴቶችም ዘርፍ ባሳለፍነው አመት በ1500 ሜትር የአለምን ሪከርድ ማሻሻል የቻለችው ጉድፍ ፀጋዬም በዘንድሮው ውድድር ለማሸነፍ ቅድሚያ ግምት ከሚሰጣቸው አትሌት መካከል በግንባር-ቀደምትነት ምትጠቀስ አትሌት ናት።

ፈለቀ ደምሴ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.