ቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በስታንፎርድ ብሪጅ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል ።
በአስራ ሶስተኛዉ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በስታንፎርድ ብሪጅ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል ።
በጨዋታው ጆርጊኒሆ በ87′ ኛው ደቂቃ የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሮ ክለቡን መሪ ቢያደርግም በ90+4’ኛው ደቂቃ ላይ ካዝሚሮ ለማንቸስተር ብ አስቆጥሮ ማንቸስተር ዩናይትድ ነጥብ ተጋርቶ እንዲወጣ አስችሎታል ።
ቼልሲ በ21 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ማንቸስተር ዩናይትድ ደግሞ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።
👉በአስራ አራተኛው የሊጉ መርሐግብር ቅዳሜ ጥቅምት 19 ቀን 11 ሰአት ላይ ቼልሲ ብራይተንን ይገጥማል።
👉ማንቸስተር ዩናይትድ ዌስትሀምን ጥቅምት 20 ቀን ማታ 1.15 ሰአት ላይ ይገጥማል ።