“THE BEST” ፉትቦል አዋርድ ሽልማት አሸናፊዎቹ ይፋ ሆነዋል።
በፊፋ አዘጋጅነት ዘንድሮ ለ 6ኛ ጊዜ የተካሄደው “THE BEST” ፉትቦል አዋርድ ሽልማት ስነ-ስርአት ተካሂዷል።
👉 በወንዶች ምርጥ ተጫዋች ዘርፍ
ፖላንዳዊው ሮበርትየግብ አዳኝ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ አሸንፏል።
👉በሴቶች ምርጥ ተጫዋች ዘርፍ
የባርሴሎናዋ አሌክሳ ፑቴላስ አሸናፊ ሆናለች። አሌክሳ የባሎንዶር አሸናፊ እንደነበረች ይታወቃል።
👉በወንዶች ምርጥ አሰልጣኝ ዘርፍ
ጀርመናዊው የቼልሲ አሰልጣኝ ቶማስ ቱኸል አሸናፏል።
👉በሴቶች ምርጥ አሰልጣኝ ዘርፍ
የቼልሲዋ አሰልጣኝ ኤማ ሄይስ አሸናፊ መሆን ችላለች።
👉በሴቶች ምርጥ ግብ ጠባቂ ዘርፍ
የቺሊ ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ የሆነችው ክርስቲያን ኤንድለር ተመርጣለች።
👉በወንዶች ምርጥ ግብ ጠባቂ ዘርፍ
ሴኔጋላዊው የቼልሲው ግብ ጠባቂ ኤድዋርድ ሜንዲ አሸናፊ መሆን ችሏል።
👉የፌርፕለይ(ስፖርታዊ ጨዋነት) ዘርፍ
የዴንማርክ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች እና የህክምና ባለሙያዎች ሆነዋል።ምክንያቱ ደግሞ ቶሎ ወደሜዳ በመግባት የክሪስታን ኤሪክሰንን ህይወት መታደግ ስለቻሉ ነው።
👉የፑስካሽ የአመቱ ምርጥ ጎል ዘርፍ
ኤሪክ ላሜላ አርሰናል ላይ ያስቆጠራት ራቦና ምት ተመርጣለች።
ሚካኤል ደጀኔ።