የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 25ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በሀዋሳ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 25ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በሀዋሳ እያከናወነ ይገኛል።
በሀገራችን በህወሀት በተከፈተው ጦርነት ሳቢያ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን በጸሎት እንዲጀመር የፌዴሬሽኑ ዋና ጸሀፊ አቶቢልልኝ በጠየቁት መሠረት በጸሎት ቀጥሎም የኢትዮጵያን ብሄራዊ መዝሙር በመዘመር የተጀመረው ጉባኤ
በአትሌት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት የመክፈቻ ንግግር የቀጠለ ሲሆን በፕሬዘዳንቷ
ግብዣ መሠረት ክቡር አቶ ቀጀላ መርዳሳ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የእንኳን ደስ ያላችሁ ንግግር በማድረግ ጉባኤውን አስቀጥለዋል።
👇 ይከታተላሉ
ሰአት 3.50 በህልውና ማስከበር ዘመቻ ለተሳተፉ እውቅና እየተሰጠ ይገኛል
👉ለአትሌት ገዛኸኝ አበራ
👉ለአትሌት ማርቆስ ገነቴ
👉አትሌት ዋና ኦፊሰር ፋንቱ ነጊሶ
10.51 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያሳተመው መጸሀፍ የምረቃ ስነስርአት እየተከናወነ ነው።….
5.05 የ2013 በጀት አመት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
የስራ አፈጻጸምና የፋይናንስ ሪፖሮት በአቶ ቢልልኝ መቆያ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽፈት ቤት ሀላፊ እየቀረበ ይገኛል….
👉የ2020 ኦሎንፒክ ውጤት ከእቅድ በታች ነው ወደፊት ከዚህ የተሻለ ምን ለመስራት ታቅዷል…..
👉 ዶክተር ዘላለም ከአማራ ክልል ከአማራ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን- ሪፖርቱ ጥሩ ነው ለሰራችሁት ስራ እናመሰግናለን …..
– የመጸሀፎቹ ህትመት እጅግ በጣም ጥሩ ነው ውስጡን ባላየውም መታተሙ ጥሩ ነው….
– እቅድ መኖሩ ጥሩ ነው ሀብት በማሰባሰብ ደረጃ ፌዴሬሽኑ የሚሰራው ጥሩ ነው
-የባለሙያ ስልጠና ላይ ቁጥሩ ያንሳል
– ሪፖርቱ ላይ እንዳየነው በጥናትና ምርምር ላይ አልተሰራም…
👉አቶ አስናቀ ከኢትዮጵያውያ ንግድ ባንክ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላሰራው ስቴዲየም ለተደረገው ድጋፍ እናመሠግናለን ….
-ሪፖርቱ ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ተገልጸዋል መፍትሄዎቻቸውም ቢገለጹ
– ለመከላከያ በሞዴልነት ላገለገሉት የተሰጠው እውቅና ጥሩ ነው
👉ነስረዲን ንጉሴ ከደቡብ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
– የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተደራጀ አሰራር አለው
ነገር ግን ክልል አካባቢ ያሉ ፌዴሬሽኖቾ ለይስሙላ ያሉም ስላሉ ከነሱ ጋር ያለው ግኑኙነት እና እገዛ ካልተሻሻለ ዋጋ የለውም የሆነ ቦታ ስታክ ያደርጋል።….
-ማርኬቲንግ ላይ ጥሩ ነው ግን ይቀራል ብዙ መሥራት ይችላል…..
👉ሌሎች ሁለት አስተያየት ስጪዎች ስለክልሎች ድጋፍና አብሮ ስለመስራት በሰፊው ሀሳብ ተሰጥተዋል ።….
👉 አብዱ
ድጋፍች አሉ ለሁሉም ክልሎች አኩል ድጋፍ ቢሰጥ ጥሩ ነው አመራሮች በአካል ተገኝተው ቢያነቃቁ ጥሩ ነው….
6.25’👉የአሰልጣኞች ተወካይ
ከክልል እና ከክለቦች ጋር በጋራ ቢሰራ ክልሎችም የሰሩትን ቢያሳውቁ ፌዴሬሽኑም ቢጠይቅ ጥሩ ነው።………
6.33👉የፌዴሬሽኑ ዋና ጸሀፊ አቶቢልልኝ ማብራሪያና መልስ እየሰጡ ነው
– የተሰጡ ሀሳቦች ገንቢዎች ናቸው ፌዴረሽኑ ክልልሎችን
ከማደራጀት ባለፈ ክልሎች ከክልል መንግስታት ጋር ተነጋግረው ፌዴሬሽኑን ቢያጠናክሩ የበለጠ የተሻለ ይሆናል
– የተጠቀምነውንም ብናመሰግን ጥሩ ነው በተለይ ቅርብ ያሉ ክልሎች ተጠቃሚዎች ናቸው ይልቁንም ራቅ ያሉ ክልሎች በበቂ ሁኔታ አልተጠቀሙም ያሉብንን ችግሮች
በሰፊው ግዜ ተይዞለት መፍትሄ ቢገኝለት ጥሩ ነው።……..
👉አቶ ተፈራ ሞላ የስራ አስፈጻሚ አባል
ተጨማሪ ማብራሪያ
– ሁሉም አካባቢ ላይ የተመጣጠነ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር በተጠና ሁኔታ በሰፊው መስራት ያስፈልጋል …….
-ኦሎንፒክ ላይ የነበሩንን ጉድለቶች የውጪ ተጽእኖዎችን
ትተን ራሳችንን መፈተሽ አለብን።….
👉አትሌት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት
-የተሰጡትን ሀሳቦችና ጥያቄዎች ባለን አቅም መሰረት ለመፈጸም እንሰራለን በተጨማሪ ሁላችንም በጋራ በመረባረብ ችግሮችን ብንቀርፍ ጥሩ ነው።…….
-ሀብትንና ገቢን በተመለከተ በተሻለ ሁኔታ እንሰራለን…
– እኛ ሁሉንም ክልል እኩል ነው የምናየው ደራርቱ ከበቆጂ
መጥታ ኢትዮጵያን ወክላ ነው የሮጠችው እንጂ ኦሮሚያን ወክላ አይደለም ….
ከቤቱ በጭብጨባ ታጅቧል
👉ክቡር አቶ ቀጀላ መርዳሳ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
– ክለብችና ክልሎች ከፌዴሬሽኑና ከመንግስት ጥገኝነት ተላቀው ራሳቸውን መቻል አለባቸው እዚህ ላይ መስራት አለብን
-በቶኪዮ ኦሎንፒክ ለነበረው ጉዳይ የጋራ መድረክ መያዝ አለበት በቀጣይ 3ወር እናከናውናለን ይህ ችግር መፈታት አለበት…..
7.30′-የእቅድ አፈጻጸም በአባላት ጸድቆ ለምሳ ተበትኗል
ከምሳ መልስ
9.00’👉የውጭ ኦዲተር ሪፖርት እያቀረቡ ነው
9.15’👉 የቀረበውን ሪፖርት የጉባኤው አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀውታል ።
9.20’👉 የፌዴሬሽኑ ዋና ጸሀፊ አቶቢልልኝ የ2014 አ/ም በጀት አመት እቅዶችን እያቀረቡ ነው።
9.48′ 👉በቀረበው በጀት ላይ ከጉባኤው አባላት ጥያቄዎች እና ሀሳቦች እየቀረቡ ነው
10.45′ ከጉባኤው አባላት ለቀረበው ጥያቄና ሀሳብ
ፌዴሬሽኑ ዋና ጸሀፊ አቶቢልልኝ ማብራሪያ እየሰጡ ነው
10.50′ 👉ዶክተር በዛብህ ወልዴ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ
ፌዴሬሽን አቃቢ ንዋይ ተጨማሪ ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
11.20′ 👉 የ2014 አ/ም በጀት አመት እቅድ በአባላቱ ጸድቆል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 25ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የሁለተኛ ቀን ውሎ
3.00 👉 የፋይናንስ ፣የንብረት የሰው ሀብት አስተዳደር መመሪያዎች በዋና ጸሀፊው በኩል እየቀረበ ይገኛል
👉በቀረበው ውይይት ላይ እየተወያዩበት ይገኛሉ
የዳኞቾ ተወካይ
-የዳኞች እና የተለያዩ ሙያተኞች ስለሚከፈላቸው አበል ማነስ ዙሪያ በአባላቱ በሰፊው ትኩረት ተሰጥቶት እየተወያዩበት ይገኛል።
-የውጪ ጉዞ አበል ለአትሌቱ እና ለባለሙያዎች ያንሳል
ልዩነቶች አሉ
5.00 👉ከተወያዮች የቀረበውን ሀሳብና ማስተካከያ በተመለከተ የፌደሬሽኑ ዋና ጸሀፊ አቶ ቢልልኝ ማብራሪያና መልስ እየሰጡ ነው።
5.25’👉 አቶ ተፈራ ሞላ የስራ አስፈጻሚ አባል የዳኞች አበል እና የውጪ ጉዞን በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
5.40 👉የተከበሩ ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ የፌዴረሽኑ ም/ፕሬዚዳንት የፋይናንስ እና አፈጻጸም መመሪያን በማንሳት ከተሳታፊዎች የቀረበውን የአበል ጥያቄ መሰረት በማድረግ
ወደፊት ስራ አስፈጻሚው ጥናት አድርጎ ቢያሻሽለው በግሌ ጥሩ ይመስለኛል ግን በጥናት እና በተሞክሮ ተጠንቶ ቢሆን ጥሩ ነው።
-ሪፎርሙን በተመለከተ ግለሰብን ያማከለ ሳይሆን ተቋማትን ያማከለ እንዲሆን ተስማምተናል ።
6.05-👉የአፋር ክልላዊ መንግስት በደረሰበት የህወሀት ጦርነት ሳይደናቀፍ የሰራቸው የስታዲየም ግንባታ እና የልማት እንቅስቃሴ በክልሉ ተወካይ ጥያቄ አጠር ያለ ቪዲዮ እየታየ ነው
6.10👉 ለክልል ፌዴረሽኖች እንደደረጃቸው የማበረታቻ
የገንዘብ ሽልማት እየተሰጠ ይገኛል።
ለክልሎች
240 ሺህ ብር ለኦርሚያ
180 አማራ
140 አአ
100 ሲዳማ
80 ደቡብ
60 ድሬዳዋ
40 ጋምቤላ
20 ሱማሌ
6.21 👉ለክለቦች እንደደረጃቸው የማበረታቻ
የገንዘብ ሽልማት እየተሰጠ ይገኛል።
300 ሺብር ለኢትዮ ኤሌክትሪክ
240 መከላከያ
180 ኦሮሚያ ፓሊስ
140 ፌድራል ማረሚያ
100 ንግድ ባንክ
80 ሲዳማ ቡና
60 ፌ ፓሊስ
ጥሩነሽ ዲባባ እና አማራ ፓሊስ 40
6.25👉 ክቡር አምባሳደር መስፍን ቸርነት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ንግግር እያደረጉ ነው
-የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የወጣቶች ስልጠና ላይ በሰፊው መስራት አለበት…
-የክልል ብ/ፌደሬሽኖችን ማብቃት አለበት እነሱም እራሳቸውን መቻል አለባቸው….
👉ዋና ጸሀፊ አቶ ቢልልኝ እና ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የምስጋናና የማጠቃለያ ንግግር አድርገው ጠቅላላ ጉባኤው ተጠናቋል።
👇👇👇
ከ ethiopisn sport ፌስቡክ ፔጅ የቀጥታ ስርጭት ላይ የተወሰደ
ፈለቀ ደምሴ
👇
https://www.facebook.com/539417222922650/posts/1828056287392064/