የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤውን በአርባንጭ ከተማ አከናወነ
ታህሳስ 23 ቀን በአርባምንጭ ከተማ ሀይሌ ሪዞርት ሲምፖዚየም በማከናወን የጀመረው
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ጠዋት ከ3 ሰአት ጀምሮ ሲከናወን ቆይቶ ተጠናቋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ በመክፈቻ ንግግራቸው ፌዴሬሽኑ ያከናወናቸውን አጠቃላይ ስራዎችና፣ ያሳካቸውን፣ እና የገጠሙትን ችግሮች ሰፋ በማድረግ ገልጸዋል።
የ2013 የዕድቅ አፈፃፀም ቀተመለከተ የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ኢንስትራክተሮችን ፣ አሰልጣኞ ፣ ዳኞች እና የህክምና ባለሙያዎችን በተመለከተ ፣የታዳጊዎችን እና ወጣቶች ልማትን ፣የአሰልጣኞች ስልጠናን ፣ የሀገር ዉስጥ ዉድድሮችን ፣ የስፖርት ማዘዉተሪያ ቦታዎችን እና ማሰልጠኛዎችን ለዉድድር ምቹ ማድረግን በተመለከተ፣ የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን ፣ በ ፣ የፌዴሬሽኑ የስፖንሰር አቅም ፣ የሰዉ ሀብትን ፣የሴካፋ ከ23 አመት በታች ዉድድርን ሁሉንም ብሔራዊ ቡድኖች በተመለከተ ሰፋ ያለ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
ከአቶ ባህሩ ሪፖርት በመቀጠልም የግዥ እና ፋይናይስ ዳይሬክተሩ አቶ ነብዩ የሂሳብ መግለጫ በሶስት ክፍሎች በመክፈል አብራርተዋል። በመግለጫቸውም
የገቢ ዝርዝሮችን ያብራሩ ሲሆን ከፊፋ 67 ሚሊዮን ከካፍ ደግሞ 10 ሚሊዮን እንዲሁም ከመንግሥት 21 ሚሊዮን የተገኘ በመሆኑ በአመቱ ውስጥ በጠቅላላው 124 ሚሊዮን ገቢ እንደነበረዉ ለጉባኤው አሳውቀዋል።
በወጪ በኩል ደግሞ ለአስተዳደር ፣
ለከፍተኛ ሊግ ፣ ለአንደኛ ሊግ ፣ ለክልሎች እና ለሴቶች አጠቃላይ 121 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር ወጪ መደረጉን ገልጸዋል።
በበጀት አመቱም ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር በትርፍነት መመዝገቡን ተገልጿል። ከ2012 አመት ሲነፃፀርም በ3ሚሊዮን ብር ዕድገት እንዳለውም ገልጸዋል።
ከዚህ በመቀጠል የውጪ ኦዲተሩ የእዲት ሪፖርት አቅርበዋል።
በመቀጠል የጠቅላላ ጉባኤው አባላት ጥያቄዎችን እና ሀሳባቸዉን እንዲያቀርቡ
አቶ ኢሳያስ ጅራ አባላቱን በመጋበዝ አባላቱም ሀሳብና ጥያቄዎቻቸውን አቅርበዋል።
ከነዚህም መካከል
በፓይለት ፕሮጀክት ዉስጥ የማቴሪያል ዕጥረት እንዳለ፣የሴቶች እግርኳስ ላይ በቂ ትኩረት እየተሰጠው እንዳልሆነ፣
የዉድድር ስፍራዎች እጥረት በታችኛው ላጎች ላይ እንዳለ፣ ፣የአደረጃጀቶች ችግር መኖሩንና አለመቀረፋን፣ በዕቅድ የመመራት ላይ ችግር መኖሩን፣ ፌዴሬሽኑ ለሰራቸውስራውች ተደጋጋሚ ሙገሳዎች ተደምጠዋል።ከባህርዳር ስታዲየም ጋር ተያይዞ የተቀጣዉ የባህርዳር ስታዲየም ሳይሆን የኢትዮጵያ ስቴዲየም ነው ነው የተቀጣው ይሄንን በተመለከተ ፌዴሬሽኑ የባህርዳር ውለታ እረስቷል በሚል ከአማራ ክልል ተወካይ የቀረበ ሲሆን ሁሉንም ጥያቄዎቸ
ጠቅለል በማድረግ አቶ ኢሳያስ መልስ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም በስራ አስፈጻሚው በኩል ከጽህፈት ቤት ሰራተኛው አቶ ሰለሞን ጋር በመመሳጠር ደብዳቤ በመጻፍ ያለስራ አስፈጻሚው እውቅና ደብዳቤ ጽፈው ኦሎንፒክ ምርጫ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉትና ኗስራ አስፈጻሚው ዕገዳ ላይ የነበሩትን የወ/ሮ ሶፊያ አልማሙን ዕገዳ
እንዲነሳ ወይም እንዲጸድቅ ለጠቅላላ ጉባኤው የቀረበለት ሲሆን እገዳው እንዲነሳላቸው ጉባኤው በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡
በጎደሉት በምክትል ፕሬዝዳንቱ አቶ አወል ቦታ ላይ ፌዴሬሽኑ በሰጠው ጥቆማ መሠረት
አቶ አበበ ገላጋይን ተመርጠዋል፡፡
የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሜቴ አባል በመሆን ደግሞ አቶ ዮሴፍ ካሳ ተመርጠዋል።
በአርባምንጭ ሀይሌ ሪዞርት ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረዉ ጠቅላላ ጉባኤም የተለያዩ ወሳኔዎች ተላልፈዉበት እንዲሁም ሪፖርቶች የፀደቁበት ሲሆን በዕለቱም በቅርቡ በሞት ለተለዩት ዶ/ር ሲራክ ሀ/ማርያም የህሊና ፀሎት ተደርጎ ጠቅላላ ጉባኤዉ ተጠናቋል።
የፌዴሬሽኑ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ መጋቢት ወር ላይ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሲሆን አጠቃላይ የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ደግሞ ሰኔ ወር ላይ በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ እንደሚደረግ ከተማው በበቂ ሁኔታ ዝግጁ ካልሆነ ለሌላ ከተማ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ፈለቀ ደምሴ
