የሮሜሉ ሉካኩ በቼልሲ ቆይታው ላይ የተናገረው አስደንጋጭ ንግግር።

ሙሉ ስሙ ሮሜሉ ሜናማ ሉካኩ ቢሊንጎሊ ሲሆን የ28 አመት የቼልሲ የፊት መስመር ተጫዋች ነው።ሜትር ከ ዘጠና ሚረዝመውና 103 ኪሎግራም ሚመዝነው ይህ ግዙፍ አጥቂበ 2011 ቼልሲ ከቤልጂየሙ አንደርሌክት ካስፈረመው በኋላ በቀጣይ አመት በውሰት ውል ወደ ዌስት ብሮምዊች አምርቶ እዛም 1 አመት ከቆየ በኋላ ወደ ኤቨርተን በማቅናት ሁለት አመት ቆይቶ ድንቅ ብቃቱን ካሳየ በኋላ ጉዲሰን ፓርክን ለቆ ማንቸስተር ዩናይትድን ተቀላቅሏል። ቀያዮቹን ከተቀላቀለ በኋላ ግን የአቋም መዋዠቅ አጋጥሞታል ከዛም 2 አመት ከቆየ በኋላ
ኦልድትራፎርድን ለቆ ኢንተርሚላንን ተቀላቅሏል።

በሳንሲሮ ጁሴፔሜዛ 2 ድንት አመታትን ከአሰልጣኙ አንቶኒዮ ኮንቴ ጋር ያሳለፈ ሲሆን ባደረጋቸው 95 ጨዋታዎች 64 ጎሎችንን ሚያስቆጥር ችሏል የስኩዴቶ ዋንጫን ከናራዙሪዎቹ ጋር ማሳካት ችሎም ነበር። ኢንተርሚላን በኮቪድ ባጋጠመው የኢኮኖሚ ቀውስ ሉካኩን ብቻ ሳይሆን የቀኝ መስመር ተከላካዩን ሞሮካዊው አርቻፍ ሀኪሚን ለመሸጥ ተገዷል። አሰልጣኙ አንቶኒዮ ኮንቴም
ይህን ተከትሎ ክለቡን ለቆ መውጣቱ ይታወሳል።

▪️ከዛም ሉካኩ 135 ሚሊዮን ዶላሮች ፈሰውበት በ2014 ክለቡን ለቆ ከሄደበት ወደ ስታም ፎርድ ብሪጅ ተመልሷል። የዘንድሮ የውድድር ዘመን በሁሉም ጨዋታዎች ለቼልሲ ባደረጋቸው 18 ጨዋታዎች 7 ጎሎችን አስቆጥሯል።ግን ከትላንት በስቲያ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የፌስቲቭ ጨዋታዎች ብራይተንን አስተናግደው ነጥብ ከጣሉ በኋላ ነው ይህ አነጋጋሪ ቃለ-ምልልስ የወጣው። ሉካኩ ከ sky italy ጋር ባደረገው ቆይታ በቼልሲ አሁን ባለው ሁኔታ ደስተኛ አይደለሁም።የቶማስ ቱኸል የአጨዋወት መንገድ ምንም አልተመቸኝም ብሏል ቃለ-ምልልሱ ከ 3 ሳምንት በፊት የተሰጠ ነው በዛ ሰአት ሉካኩ ከጉዳት መልስ ነበር እና ቱኸልም በጥንቃቄ እያየ እየተቀየረ እንዲገባ ነበር ሚያደርገው 4 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በዚ መልኩ አካሂዶ ነበር ግን ቃለ-ምልልሱ የወጣው አሁን ነው ሉካኩም ይቀጥላል።

እኔ ደና ነኝ ምንም ችግር የለብኝም ግን እዚ ባለው ሁኔታ ደስቸኛ አይደለሁም ቱኸል የተለየ አይነት አጨዋወት ነው ያለው ግን እኔ ፕሮፌሽናል ተጫዋች ስለሆንኩ ተስፋ አልቆርጥም ብሏል። ለኢንተርሚላን ደጋፊዎችም ይቅርታውን ጠይቋል። ባሳለፍነው ክረምት የተፈጠረውን ነገር በዛ መልኩ መሆን አልነበረበትም።ኢንተርሚላንን የለቀኩበት መንገድ ትክክል አይደለም በትክክለኛው ሰአት አይደለም ሳንሲሮን የለቀቅኩት ግን ስመረቴን ለመግለፆ አሁን ትክክለኛው ሰአት ነው።ደጋፊዎቹ ለኔ እና ለቤተሰቤ ያደረጉልኝን መቼም ቢሆን አልረሳውም ኢንተር ሁሌም ልቤ ውስጥ ነው።ከልቤ የምመኘው ነገር የእግርኳስ ህይወቴ ከመጠናቀቁ በፊት ጥሩ አቋም ላይ እያለሁ ኢንተርሚላንን ዳግም ተመልሼ ዋንጫዎችን ማንሳት እፈልጋለሁብሏል ሮሜሉ ሉካኩ።

ከ11 አመት በኋላ ኢንተርሚላንን የስኩዴቶ ዋንጫ እንዲያነሳ ካደረጓቸው ተጫዋቾች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠራው ይህ ተጫዋች ነው።እናም የኢንተርሚላን ደጋፊዎች ይቅርታ መጠየቁ እና ባጠቃላይ ባደረገው ንግግር የቼልሲ ደጋፊዎች ደስተኛ አይደሉም ቁጣም ሊያስነሳ እንደሚችል ይገመታል።ቶማስ ቱኸልም ምን አይነት እርምጃ ይወስድበታል ወይስ ባላየ፣ባልሰማ ነገርችን ያልፋል ሚለውም ሌላ ተጠባቂ ነገር ነው።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.