28 ጎሎች የዘነቡበት የቦክሲንግ ዴይ ጨዋታዎች።
▪️የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ላይ ሲደርስ የበአል ማግስት የቦክሲንግ ዴይ ጨዋታዎች ትላንት ተካሂደዋል።
▪️ቀደም ብሎ የሊድስ እና የሊቨርፑል ጨዋታ እንዲሁም የዎልቭስ እና የዋትፈርድ ጨዋታዎች በኮቪድ ኦሚክሮን ቫይረስ ምክንያት ቀድመው ለሌላ ጊዜ የተላለፉ ጨዋታዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ጨዋታዎች በተያዘላቸው እቅድ መሠረት የተከናወኑ ጨዋታዎች ናቸው።
▪️ሌስተር ሲቲ ወደ ኤቲሀድ አቅንቶ የሊጉ አናት ላይ የተቀመጡትን ማንቸስተር ሲቲዎችን አግኝተው 6-3 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል። ጄሚ ቫርዲን ወደ ተቀያሪ ወንበር አውርደው ጨዋታውን የጀመሩት የሌስተሩ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ ዳኝነቱ ላይ ጥያቄአንስተዋል። ይህ ጨዋታ በ1991 ማንየስተር ዩናይትድ ኦልድሀምን 6-3 ካሸነፈ በኋላ ብዙ ጎሎች የታዩበት የቦክሲንግ ዴይ ጨዋታ ሆኗል።
▪️አርሰናል ወደ ካሮው ሮድ አቅንቶ በሰፊ የጎል ልዩነት 5-0 አሸንፏል። አሁንም ኦባምያንግን ከስብስቡ ውጪ አድርጎ የጀመረው ሚኬል አርቴታ ድል ቀንቶታል በጨዋታው 2 ጎሎችን ማስቆጠር የቻለው የ20 አመቱ ቡካዮ ሳካ በእድሜ ትንሽ ሆኖ 10 የፕሪሚየር ሊግ ጎሎችን ያስቆጠረ 2ኛው ተጫዋች መሆን ችሏል።
▪️ሌላ 1 ጎል ከመረብ ያሳረፈው ኤሚል ስሚዝ ሮ በ 3 ተከታታይ ጨዋታዎች ተቀይሮ እየገባ ጎል ማስቆጠር ችሏል። ከዚ በፊት 2009 ቶማስ ሮዚስኪ እንዲሁ ተቀይሮ እየገባ ጎል ካስቆጠረ በኋላ በአርሰናል ቤት የመጀመሪያው ተጫዋች መሆን ችሏል።
▪️የአንቶኒዮ ኮንቴው ቶተንሀም በመነቃቃት ላይ እንደሆነ ሚያሳይ ውጤት አስመዝግቧል።ትላንት የደቡብ ለንደን ክለብ የሆነውን ክሪስታል ፓላስን በሜዳቸው ጋብዘው 3-0 አሸንፈዋል።
▪️እዚ ጨዋታ ላይ ዊልፈርድ ዛሀ የቀይ ካርድ ሰለባ ሆኗል። ይህ አይቮሪኮስታዊ ተጫዋች እ.ኤ.አ በ 2010 ለክሪስታል ፓላስ የመጀመሪያ ጨዋታውን ማካሄድ ከቻለበት ጊዜ አንስቶ እስከ ትላንት ጨዋታ ድረስ በአጠቃላይ 5 ቀይ ካርዶችን አይቷል። በግልፍተኝነቱ ሚታወቀው ይህ ተጫዋች በቦክሲንግ ዴይ ቀይ ካርድ ያየ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
▪️ዌስትሀም ባልተጠበቀ መልኩ በሳውዝሀምፕተን 3-2 ተሸንፏል። 2 ጊዜ ከመመራት እየተነሳ አቻ ማድረግ ቢችልም የዌስትሀም ቡድን በ3ኛው ግብ እጅ ሰጥቷል። በጨዋታው 1 ጎል ያስቆጠረው እና 1 ጎል አመቻችቶ ማቀበል የቻለው ጄምስ ዋርድ ፕራውስ 10 እና ከዛ በላይ የሆኑ የፕሪሚየር ሊግ ግቦችን ከፍፁም ቅጣት ምት ወይም ከቆመ ኳስ ብቻ ያስቆጠረ 4ኛው ተጫዋች ሆኗል። ቲዬሪ ሄንሪ ፣ ኢያን ሀርተን ፣ እና ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በመከተል ማለት ነው።
▪️የቶማስ ፍራንኩ ብሬንትፈርድ ወደ አሜክስ አቅንቶ በግራም ፖተሩ ብራይተን ሆቭ አልቢዮን 2-0 ተሸንፈዋል። ትሮሳርድ እናየቀድሞ ተጫዋቻቸውኒል ሞፔይ የጎሎቹባለቤቶች ናቸው።
▪️በመጨረሻም ቼልሲ ወደቪላ ፓርክ በማቅናት አስቶንቪላን 3-1 አሸንፏል። 2 ጎሎችን በፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠር የቻለው ጣልያናዊው ጆርጂንሆ ቶማስ ቱኸል ቡድኑን ከ ፍራንክ ላምፓርድ ተረክቦ በጥር ወር ላይ የመጀመሪያውን ጨዋታ መምራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ቡድኑ 11 የፍፁም ቅጣት ምቶችን አግኝቷል ጆርጂንሆ ደግሞ 9ኙን ከመረብ ጋር ማዋሀድ ችሏል። በአጠቃላይ በፍጹም ቅጣት ምት ከተገኙት 25 እድሎች 22ቱን አስቆጥሯል።
▪️ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ተቀይሮ የገባው ግዙፉ አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩ 1 ጎል ሲያስቆጥር 1 ጎል ሚሆን ፍፁም ቅጣት ምት ዕድል አስገኝቷል። ይህ ግዙፍ አጥቂ 90 ሚሊዮን ፓውንድ ወቶበት ስታም ፎርድ ብሪጅ የመጣ ሲሆን የትላንት እንቅስቃሴው አመርቂ እንደነበር አሰልጣኙም ገልፀዋል።
▪️ጨዋታዎቹ ዛሬም ሲቀጥሉ አዲስ አሰልጣኝ ኤዲ ሀውን ሾመው ግን ውጤት ቀውስ ውስጥ ሚገኙት ኒውካስል ዩናይትድ ማንቸስተር ዩናይትድን ምሽት 5:00 በሴንት ጄምስ ፓርክ ሚያስተናግዱ ይሆናል።
▪️ነገም በርካታ ጨዋታዎች ሲካሄዱ ዎልቭስ ከ አርሰናል ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ አሰልጣኝ ብሩኖ ላዥ ቡድናቸው ውስጥ ብዙየኮቪድ ተጠቂ ስላለ እንዲተላለፍላቸው በጠየቁት መሠረት ተላልፏል።
ሚካኤል ደጀኔ።