15ኛው የአዲስአበባ ሲቲ ካፕ ፍፃሜውን አገኘ።

▪️በ አበበ ቢቂላ ስቴዲየም ለመካሄድ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የ ባህርዳር ከነማ ና የ መከላከያ የ ፍፃሜ ጨዋታ በ አማራ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ገቢ ማሰባሰቢያ እንዲሆን ታስቦ ሜዳውን እንዲሁም የሽልማት ፕሮግራሙን ወደ ባህርዳር ኢንተርናሽናል ስቴዲየም ማዞሩ ይታወሳል።
▪️4ቱም ቡድኖች ማለትም ለደረጃ ሚጫወቱት ጅማ አባ ጅፋር እና ቅ/ጊዮርጊስ እንዲሁም ለፍፃሜው የተገናኙት ባህርዳር ከነማ እና መከላከያ ሁሉም ተስማምተው ነው ወደ ባህርዳር ያቀኑት።
▪️ቀደም ሲል 8:00 ላይ ቅ/ጊዮርጊስ ከ ጅማ አባ ጅፋር ለደረጃ የተጫወቱ ሲሆን መደበኛ 90 ደቂቃውን 2 አቻ በሆነ ውጤት ያጠናቀቁ ሲሆን ወደ መለያ ምት አምርተዋል። በዚህም መሠረት ቅ/ጊዮርጊስ 5-4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የ 3ኛ ደረጃነቱን አረጋግጧል።
▪️የደረጃ ጨዋታ መጠናቀቁን ተከትሎ 10:15 ላይ የጀመረው የፍፃሜ ጨዋታ ጥሩ እንቅሰቃሴ የታየበት ነበር።የ ዮሀንስ ሳህሌው ቡድን በግማሽ ፍፃሜው ከ ቅ/ጊዮርጊስ ጋር ሲጫወቱ በ አብዛኛው በመከላከሉ ላይና ኳሶችን ማጨናገፍ ላይ ተኩረት አርገው ወደ ሜዳ መግባታቸው ይታወሳል።በ ዛሬው ጨዋታ ግን ከራሳቸው ሜዳ በመውጣት ተጋጣሚ ላይ ጫና ለመፍጠር ሞክረዋል።
▪️በኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ የሚመራው ባህርዳር ከነማ ቡድን ኳሶችን በጥሩ ሁኔታ በመቀባበል የተጋጣሚን ቡድን የተከላካይ መስመር ሰብሮ ለማለፍ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደርግ ተስተውሏል። ሙከራውም ተሳክቶ በ 43 ደቂቃ ላይ ተመስገን ደረሰ የጣናው ሞገድን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል።
▪️በዚህች ብቸኛ ግብ ባህርዳር ከነማ መከላከያን ሲያሸንፍ 15ኛውን የአዲስአበባ ሲቲ ካፕ ዋንጫ ከፍ አደርጎ ማንሳት ችሏል።
▪️ ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ ባህርዳር ከነማን የአዲስ አበባ ክለብ ሳይሆን ዋንጫውን ያነሳ የመጀመሪያው ክለብ አድርገውታል።
#ሚካኤል_ደጀኔ
