የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ፍፃሜውን አገኘ።
- ▪️የ አውሮፖ ኔሽንስ ሊግ እ.ኤ.አ በ 2018 የአለም ዋንጫ ከተጠናቀቀ በኃላ የተመሠረተ ሲሆን በየ ሁለት አመት ልዮነት ለመካሄድም ያቀደ ነበር።በዛው አመት ፖርቹጋል ዋንጫውን ከፍ ማድረግ ችላ ነበር።አምና በ ኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል።
▪️ኔሽንስ ሊግ 55 የአውሮፓ ሀገራትን በምድብ ተከፋፍለው ጨዋታቸውን ሚያከናውኑበት መድረክ ነው። ይህ መድረክ መገባደጃው ላይ ሁለት በእግር ኳሱ ሀያል የሆኑ ክለቦችን ይዞ ቀርቧል።
▪️የአለም ዋንጫ አሸናፊዋ ፈረንሳይ በ ሊዊስ ኤንሪኬ ጥሩ እንቅስቃሴ እና ለውጥ ማምጣት የቻለችውን ስፔን ጋር ጨዋታቸውን በ ጣልያኗ ሚላን ከተማ ሳንሲሮ ጁሴፔ ሜዛ ስቴዲየም ላይ አከናውነው ነበር።
▪️ፈረንሳይ ቤልጂየምን ከኋላ በመነሳት አሸንፋ እዚ ስትደርስ ስፔንም በጠንካራ የተከላካይ ክፍሏ ምትታወቀውን ጣልያንን አሸንፋ ነው ለ ዋንጫው ጨዋታ የበቃችው።
▪️ኢንግሊዛዊው አንቶኒ ቴይለር በመሩት በዚ ጨዋታ የዲዲዬ ዴሻንፕ ቡድን ቀዝቀዝ ብሎና ከኳስ ጀርባ አፈግፍገው ሲጫወቱ ተስተውሏል።በአንፃሩ የልዊስ ኤንሪኬው ቡድን ኳስ በመያዝ እና በማንሸራሸር እንዲሁም አልፎ አልፎ ሙከራዎችን በማድረግ የተሻሉ ቡድኖች ነበሩ።
▪️ራፋኤል ቫራን በ 43 ደቂቃ በጉዳት ሜዳውን ለቆ ሲወጣ በክረምቱ ሌፕዚግን ለቆ ባየርሙኒክን የተቀላቀለው ኡፖሜካኖ ተክቶት ገብቷል።አንቷን ግሪዝማን 100ኛ ጨዋታውን ለሀገሩ ያደረገበት ጨዋታ ነበር።
▪️ከዕረፍት በኋላ በ 64ደቂቃ ኦርያዛባል ሀገሩን ቀዳሚ አድርጎ ነበር ግን መሪነቱ ለ 107 ሰከንድ ብቻ ነው ሊዘልቅ የቻለው። የሪያል ማድሪዱ ፊት መስመር አጥቂ ካሪም ቤንዜማ ሀገሩን አቻ አድርጎል።
▪️በ2ኛው አጋማሽ የፈረንሳይ የግራ ተመላላሽ ተከላካዩ ቲዮ ሄርናንዴዝ የተሰጠውን ነፃነት ተጠቅሞ ወደፊት በመሄድ ለ ኪሊያን ምባፔ ኳሱን አመቻችቶ አቀብሏል ምባፔም በ 80ኛው ደቂቃ ሀገሩ ምትመራበትን ግብ አስቆጥሯል።
▪️ኪሊያን ምባፔ በ ኔሽንስ ሊጉ ከግማሽ ፍፃሜ ጀምሮ 2 ጎል 2 አሲስት በማድረግ በጣም ጠቃሚ ተጫዋች መሆኑን አሳይቷል።
▪️ፈረንሳይ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደውን የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፋለች።
ሚካኤል ደጀኔ