“ሮናልዶን ወደ ሪያል ማድሪድ መመለስ ይቻላል” ዚዳን

” ሮናልዶን ወደ ሪያል ማድሪድ መመለስ ይቻላል ” ዚዳን

ሰኞ እለት በሩን ለሮናልዶ መመለስ የከፈተው ዚነዲን ዚዳን ስለተጫዋቹ መመለስ ሲጠየቅ ሊሆን ሚችል ነገር ነው ግን ተጫዋቹን እና ክለቡን ማክበርም አለብን አሁን የጁቬንቱስ ተጫዋች ነው።ተመልሶ ቢያሰለጥነው ሚል ሀሳብ ሲነሳለት ደግሞ ከዚህ በፊት ማድረግ ያለብኝን አድርጌያለሁ ወደፊት ደግሞ ሚሆነውን እናያለን ብሏል።
የስፔን ሚድያዎች ሮናልዶ ብዙ ክብሮችን ወደ ተቀዳጀበት ማድሪድ ይመለሳል ሲሉ ቆይተዋል በ2018 በ100 ሚልዮን ዩሮ ከመሸጡ በፊት 9 ስኬታማ አመታትን በክለቡ አሳልፏል።
በባለፈው ሳምንት የለጠፈው የፌስቡክ መልክት ነው እነዚህን ጥያቄዎችን ያስነሳው መልክቱም ላይ “….. እውነት ነው ያለፈው ነገር ለሙዚየም ነው ሚገባው እላለሁ ነገር ግን እግር ኳስ ማስታወሻ አለው እኔም አለኝ …..” የሚል ነበር ይህም ጁቬንቱስ በፓርቶ ከቻምፒየንስ ሊግ ከተሰናበቱ በኃላ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.