ሊቨርፑል አሸነፈ ዦታ ዎልቭስ ላይ አገባ

ሊቨርፑል አሸነፈ ዦታ ዎልቭስ ላይ አገባ

በዎልቭስ ሜዳ ሞሊኖክስ የተደረገው የትናንት ምሽቱ ጨዋታ በሊቨርፑል 1-0 አሸናፊነት ሲያልቅ ብቸኛዋን ጎል የቀድሞው የዎልቭስ ተጫዋች ዲዮጎ ዦታ አስቆጥሯል።በዚህም ሊቨርፑል 4ቱ ውስጥ ሆኖ የውድድር አመቱን ለመጨረስ ሚያደርገውን ግስጋሴ አለምልሟል።

ለባለሜዳዎቹ ከሽንፈቱ በላይ አስከፊ የሆነው የግብ ጠባቂያቸው ሩዪ ፓትሪሺዮ የጭንቅላት ጉዳት ነው ከራሱ ተጫዋች ኮነር ኮዲ ጋር በመጋጨቱ ሜዳ ውስጥ ለ15 ደቂቃ ህክምና ሲደረግለት ቆይቶ በስትሬቸር ከሜዳ ወጥቷል።ዎልቭስ ከዚህ በፊትም በጥቅምት ከአርሰናል በነበረው ጨዋታ ኮከብ ግብ አስቆጣሪያቸውን ራዉል ሄመኔዝን በተመሳሳይ የጭንቅላት ጉዳት ከሜዳ አጥተውታል። ቡድኑም የሄመኔዝ መጎዳት ከዛም በፊት ዦታን መሸጣቸው ቡድኑ ፊት መስመር ላይ እንዲቸገር አድርጎታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.