በቤት-ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ችሏል
በ13ተኛ ሳምንት የቤት-ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ችሏል።በጨዋታው ላይ አዳማዎች በአብዲሳ ጀማል በ39ኛው ደቂቃ ቀዳሚ መሆን ችለው ነበር ቢሆንም ከእረፍት መልስ አቡበከር ናስር
በ58ኛው እና በ88ኛው ደቂቃ በጨዋታ 78ኛው ደቂቃ ደግሞ በፍፁም ቅጣት ምት ሶስታ ሲሰራ በ90ኛው ደቂቃ ታፈሰ ሰለሞን ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው 4-1 በሆነ ውጤት ሊያልቅ ችሏል።
አዳማ ከተማ አሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤልን በዘንድሮ ዓመት ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሹሞ ነበር። ቡድኑ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ቡና ሽንፈት ካስተናገደ በኃላ አሰልጣኝ አስቻለው በሰጡት አስተያየትም በገዛ ፍቃዳቸው ራሳቸውን ከኃላፊነት ማንሳታቸውን ተናግረዋል።
አሰልጣኙ ከጨዋታው በፊት ራሳቸውን ለማግለል ወስነው የነበረ ቢሆንም ከአመራሮች ጋር ተነጋግረው ለዚህ ጨዋታ እንደቀረቡ ከጨዋታው በፊት ለሱፐር ስፖርት በሰጡት አስያየት ላይ ጠቁመው ነበር።

ingrdor 1aedd1d5d3 https://wakelet.com/wake/g6QS7r1BxAcT1GEV_LZdl