የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውድድር ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ

የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፊታችን እሁድ የካቲት 14 ቀን በሚጀምረው አመታዊ የመክፈቻ ውድድር አስመልክቶ ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን ከጋዜጠኞቹ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የፌዴሬሽኑ ም/ፕሬዝዳንት አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ የስራ አስፈፃሚ አባል እና የውድድር ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ተመስገን እና የሥራ አስፈፃሚ አባል እና የማርኬቲንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ  አቶ ደረጄ አረጋ ተገኝተዋል

ምክትል ፕሬዝደንት አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ የጋዜጣዊ መግለጫው የመጠራቱ ምክንያት በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት  ሲናገሩ  ” አዲስ ሥራ አስፈፃሚዎች እንደመሆናችን መጠን ከእናተ ጋር ትውውቅ ማድረግ እንፈልጋለን። ወደ ዚህ ኃላፊነት የመጣነው የአዲስ አበባ እግርኳስ ለማሳደግ ነው። በቀጣይ እሁድ የካቲት 14 ቀን ለምንጀምረው የመክፈቻ ውድድር ያለ በመሆኑ ይህን አውቃቹሁ ሽፋን ልትሰጡን ይገባል። ውድድርን የሚያደምቀው ሚዲያ ነው። ያለ ሚዲያ ውድድር ባዶ ነው። እየደከመ የመጣውን የአዲስ አበባ እግርኳስን እንዲነቃቃ ለማድረግ የእናተ እገዛ በጣም አስፈላጊ ነው። በማንኛውም መልኩ ለምንሰራቸው ሥራዎች ከጎናችን በመሆን እንድታግዙን አደራ እንላለን ” ብለዋል።

በመቀጠል የውድድር ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አንተነህ ተመስገን እሁድ የሚካሄደውን የመክፈቻ ፕሮግራም አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በገለፃቸውም

” በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር ከ98 በላይ ክለቦች ይገኛሉ። በከፍተኛ ዲቪዚዮን በአንደኛ ዲቪዚዮን በሴቶች በታዳጊዎች በአጠቃላይ 31 ቡድኖች ስር 875 ስፖርተኞችን አቅፎ የያዘ ትልቅ ፌዴሬሽን ነው። የፊታችን እሁድ የኮቪድን ፕሮቶኮል በጠበቀ መልኩ ውድድሮችን ከጠዋቱ 02:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከፍተኛ የስፖርት ኮሚሽን አመራሮች የክፍለ ከተማ ስራ  አስፈፃሚዎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ስነ ሥርዓት እንደሚካሄድ ገልፀዋል።”

 

በማስከተል በዕለቱ የተገኙ የስፖርት ጋዜጠኞች አማካኝነት በመድረኩ ለተገኙት የፌዴሬሽኑ ተወካዮች ጥያቄዎችን ቀርቦላቸዋል።

ውድድሩ የሚጀመርበት ጊዜ ለምን ዘገየ ?

የኮቪድ ፕሮቶኮል ጠብቆ ይካሄዳል ሲባል እንዴት ነው ?

በውድድሮቹ ላይ ተመልካች ይገኛል ?

የሲቲ ካፕ ውድድር ዘንድሮ አለመኖር የፋይናስ ችግር ያጋጥማቸዋል ወይ ውድድሮችን በሲቲ ካፕ ገቢ እንደምታካሄዱ ?

የገቢ ምንጭ ለመፍጠር ስፖንሰር ላይ ምን ለመስራት አስባችኃል ?

ለተጠየቁት ጥያቄዎች በቅድመ ተከተል ከመድረኩ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በመጀመርያ አቶ አንተነህ ተመስገን ሲናገሩ

” የኮቪድ ፕሮቶኮልን በተመለከተ የተለየ ነገር አናደርግም። ሆኖም በሀገር አቀፍ ደረጃ ውድድሮች በሚመሩበት አግባብ የኛም ውድድሮች በዛ መልኩ ይካሄዳሉ።

” የተመልካች ሁኔታ ጨዋታዎቹ በዝግ ነው የሚደጉ ሲሆን ከአስር እና ከአስራ አምስት በላይ ደጋፊዎች ብቻ እንዲገቡ ይደረጋል።

“የጊዜው ጉዳይ እውነት ነው ዘግይቷል። ይህ የሆነበት ምክንያት አዲስ ስራ አስፈፃሚ በመሆናችን እና የኮቪድ ፕሮቶኮል ለመጠበቅ በምንሄድበት መንገድ ክለቦች ካላቸው የአቅም ውስንነት አንፃር መፍትሔ ለመፈለግ በምናደርገው ጥረት ውስጥ ጊዜውን ተሻምቶብናል።” በአጠቃላይ የተሳታፊ ክለቦችን ቁጥር ገድበን መንቀሳቀሳችን ካለው ሁኔታ አንፃር መሆኑን አብራርተዋል።”

” ከስፖንሰር እና ከገቢ አንፃር ምላሽ የሰጡት የፌዴሬሽኑ ማርኬቲንግ ክፍል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ደረጄ አረጋ ሲናገሩ

” የፌዴሬሽኑን አቅም በገቢ ለማጠናከር ስፖንሰር ለማግኘት ከፍተኛ ጥረቶች እየተደረጉ ናቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.