ማንችስተር ሲቲ! ጣፋጭ ድል አስመዘገበ

ማንችስተር ጣፋጭ ድል አስመዘገበ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ መርሐ ግብር ጥር 11 ቀን ምሽት 5 ሰአት የተደረገ ጨዋታ ሲጠናቀቅ ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ2 በማሸነፍ ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል ።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ በ53ኛው ደቂቃ ሪያድ ማህሬዝ በ63 ኛውና በ90ኛው አልቫሬዝ በ51ኛው ደቂቃዎች ሲያስቆጥሩ የቶተንሀም ግቦች ኩሉሴቭስኪ በ44ኛው እና ሮያል በ45+2 ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል።

ማንችስተር ሲቲ 4 – 2 ቶተንሀም
⚽️አልቫሬዝ 51′ ⚽️ኩሉሴቭስኪ 44′
⚽️ሀላንድ53′ ⚽️ሮያል 45+2′
⚽️ማህሬዝ 63′
⚽️ማህሬዝ 90′

ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ከአርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት አጥብቧል።

በሊጉ መሪዎች በተከታታይ የተሸነፈው ቶተንሀም በሰላሳ ሶስት ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከዎልቭስ እንዲሁም ቶተንሀም ከ ፉልሀም ይጋጠማሉ።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.