ጋቶች ፓኖም ለወላይታ ዲቻ ለመጫወት ተስማቷል
በሀገር ውስጥ እና ከኢትዮጵያ ውጭ በመጫወት የምናውቀው ግዙፉ አማካይ ጋቶች ፓኖም ለወላይታ ዲቻ ለመጫወት ተስማቷል።
ጋቶች በአሁኑ ሰዓት ወላይታ ዲቻን ለመቀላቀል አርባምንጭ ደርሷል። ከሰዓት ከቡድኑ ጋር ልምምድ በመስራት ቆይታ ካደረገ በኃላ ቅድመ ስምምነቱ መጋቢት ወር ሲፀድቅ ወደ ጨዋታ እንደሚመለስ ታውቋል።
በኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ጋቶች ቡናማዎቹን ከለቀቀ በኋላ ወደ ሩሲያው ክለብ አንዚ ማካቻካላ አምርቶ ብዙም ቆይታን ሳያደርግ ወደ ሀገር ውስጥ ተመልሶ በመቐለ 70 እንደርታ ስድስት ወራትን ከቆየ በኋላ በግብፆቹ ኤል ጎውና እና ሀራስ ኤል ሁዳድ እንዲሁም ወደ ሳውዲ አረቢያ ዲቪዥን ሁለት ክለብ አል-አንዋር አምርቶ መጫወቱ ይታወቃል።
