ጉዳፍ ፀጋይ የ1500 ሜትር የአለም ክብረወሰንን ሰበረች

በሴቶች 1500 ሜትር በተደረገ ውድድር ደግሞ  ጉዳፍ ፀጋይ ፈረንሳይ በተካሄደ የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አዲስ የአለም ክብረወሰን አስመዝግባለች።

አትሌቷ በፈረንጆቹ 2014 አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በካርልስሩህ ያስመዘገበችውን ክብረወሰን በ2 ሰከንድ በማሻሻል ርቀቱን በ3:53.09 ማጠናቀቅ ችላለች።

በፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው የአለም አትሌቲክ የቤት ውስጥ ውድድር 3,000 ሜትር ወንዶች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከ አንድ እስከ አራት ተከታትለው መግባት ችለዋል ።
ጌትነት ዋለ 7:24.98 በሆነ ደቂቃ በመግባት ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅቅ ሰለሞን ባረጋ ፣ ለሜቻ ግርማ እና በሪሁ አረጋዊ ተከታዩን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ሲችሉ ወርቁ ታደሰ ብስድስተኛነት ውድድሩን ማጠናቀቅ ችሏል።

   በፈረንሳይ በተደረገ ሌላ የሴቶች የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ለምለም ሐይሉ በ 3,000 ሜትር በ 8:32.55 በሆነ ደቂቃ በመግባት ውድድሯን በበላይነት አጠናቃለች ።

ለምለም ሐይሉ ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷት የነበረችውን ትውልደ ኢትዮጵያዊት ሲፈን ሀሰን በመብለጥ ነው ።

• ለምለም ሀይሉ ውድድሯነወ በበላይነት ስታጠናቅቅ የግሏን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ ጭምር ነው ።

• በዚሁ በተካሄደ የሴቶች ውድድር በ 800 ሜትር ሴቶች ሀብታሙ አለሙ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች ።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.