የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ወደ መቐለ ለታዳጊ ተማሪዎች ድጋፍ ላከ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ወደ መቐለ ለታዳጊ ተማሪዎች ድጋፍ ላከ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በትላንትናው እለት ለትግራይ ክልል ታዳጊ ተማሪዎች የሚሆኑ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ወደ መቐለ መላኩን አስታውቋል።

ክለቡ 50 ሺ ደብተሮችን እና 10 ሺ እርሳስ እና እስክርቢቶ ወደ መቐለ የላከ ሲሆን የፊታችን ሃሙስ ለትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር በመቐለ ከተማ ርክክብ እንደሚደረግ አሳውቋል።

ይህ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የተደረገ የመጀመሪያው ሰብአዊ ድጋፍ መሆኑን እና ክለቡ ወደፊት አቅም በፈቀደ መጠን ድጋፉን የሚቀጥል መሆኑን በፌስቡክ ገፁ (St. George S.A) አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.