ቶማስ ቱሄል በአሸናፊነታቸው ቀጥለዋል
የለንደኑ ክለብ ቼልሲ በ ሜሰን ማውንት እና ጆርጂንሆ ጎሎች በወራጅ ቀጠናው የሚገኙትን ሼፍልድን በማሸነፍ በድል ጉዞ ቀጥለዋል ።
• ጆርጂንሆ አምሰት እና ከዚያ በላይ ጎሎችን በአንድ የውድድር ዓመት ሲያስቆጥር ከሰባት አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ።
• ጆርጂንሆ ስድስት ጎሎችን ካስቆጠረው ታሚ አብርሀም በመቀጠል በሊጉ ለቼልሲ ብዙ ጎል ያስቆጠረ ተጫዋች ሆኗል ።
• ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲዎች ከ አምናው ሻምፒዮን ሊቨርፑል በአንድ ነጥብ እንዲሁም ከ ማንችስተር ዩናይትድ በስድስት ነጥብ ርቀው ይገኛሉ ።