ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን 5ለ0 አሸነፈ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን 5ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ለኢትዮጵያ ቡና አቡበከር ናስር በ59ኛው፣ በ64ኛው እና 82ኛው ደቂቃ ላይ ጎል በማስቆጠር ሀትሪክ የሰራ ሲሆን ሐብታሙ ታደሰ በ67ኛው ደቂቃ እንዲሁም አስራት ቱንጁ በ90ኛው ደቂቃ ላይ ጎሎችን አስቆጥረዋል።
ክውጨዋታው ምውጠናቀቅ በኋላ በቤት ኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ በ20 ነጥብ እና በ10 የጎል ልዩነት የደረጃ ሰንጠረዡን ኢትዮጲያ ቡና በሁለተኛ ነት መምራት ሲችል ተጋጣሚው ሲዳማ ቡና ደግሞ በ11 ነጥብ እና በዘጠኝ የጎል እዳ በስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በዛሬው ዕለት ጠዋት በተካሄደው የሊጉ 11ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዲያ ሆሳዕና ከቅዱስ ጊዮርጊስ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.