ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን አስደናቂ ድል አስመዘገቡ

በኮሎምቢያ ካሊ የአለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ በ5000ሜ በወንዶች የፍጻሜ ውድድር ጀግናው ወጣት አዲሱ ይሁኔ በ14:03.05 በሆነ ሰዓት ቀዳሚ በመሆን  ለኢትዮጵያ ወርቅ ገቢ በማድረግ ሀገሩን ከፍ አድርጓል።

 

ሌላኛው ጀግና ገበየሁ በላይ በ14:04.55 በሆነ ሰዓት 4ኛ በመሆን ዲፕሎማ አስገኝቷል።

በዚህ ውድድር ብርቱ ተፎካካሪ የነበሩት ኤርትራውያኑ መርሀዊ መብራቱ በ 14:03.3ሰአት ሁለተኛ
ሀብቶም ሳሙኤል በ14.03.67 ሰአት ሶስተኛ በመሆን ለሀገራቸው የብር እና የነሀስ ሜዳሊያ አስገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.