ገንዘቤ ዲባባ በስፔን ባርሴሎና የተደረገውን የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር አሸነፈች
በባርሴሎና በተካሄደ ሌላ የ 5 ኪ.ሜ ውድድር ገንዘቤ ዲባባ ታናሽ እህቷን አና ዲባባን በማስከተል በ ከርሳ ዴል ናሶስ ስፔን 15:00 በሆነ ጊዜ በመግባት ውድድሯን በበላይነት አጠናቃለች ። ታናሽ እህቷ አና ዲባባ ደግሞ 16 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ውድድሩን በማጠናቀቅ ሁለተኛ ወጥታለች፡፡
የ5 ኪሎ ሜትሩ ርቀት በትውልድ ኢትዮጵያዊት በዜግነት ሆላንዳዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን የተያዘውን 14:44 ሪከርድ ገንዘቤሪከርድ ትሰብራለች የሚል ግምት ቀደም ሲል ተሰጥቷት እንደነበር ከዚህ በፊት በሰራነው ዘገባ ላይ አስፍረን ነበር።