የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሄራዊ ቡድን በሴካፋ ዋንጫ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀቀ

በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ዋንጫ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን በማሸነፍ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ17 ዓመት በታች የሶስተኛ ደረጃ ለመያዝ ከጅቡቲ ጋር ባደረገው ጨዋታ 5 ለ 2 አሸንፏል፡፡

⚽️⚽️18′ 35′ ዮዳሄ ዳዊት
⚽️ 36′ በረከት ብርሀኑ
⚽️⚽️ 59′ 72′ በረከት ራህመቶ ለኢትዮጲያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ሲያስቆጥሩ፤

⚽️ 56′ አዩብ መሐመድ
⚽️ 77′ አዩብ መሐመድ ለጅቡቲ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም ኢትዮጲያ የሶስተኛ ደረጃን ማግኘት ስትችል ጅቡቲ ደግሞ በአራተኛ ደረጃን በማግኘት ውድድሩን ጨርሰዋል

በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ታዛኒያ ከኡጋንዳ የዋንጫ ተፋላሚ ናቸው።

ብሄራዊ ቡድኑ ከታንዛኒያ ቻው ጋር በነበረው ጨዋታ 90 ደቂቃው በ1 ለ 1 በሆነ በመጠናቀቁ ቡድኖቹ ወደ መለያ ምት ሄደው

በመለያ ምቱ የታንዛኒያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን 4 ለ 3 አሸንፎ ወደ ፍፃሜ ማለፍ ሲችል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ17 ዓመት በታች ደግሞ ከፍፃሜ ጨዋታው ውጭ መሆኑ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.