ኢትዮጵያ ቡና የፊፋን ውሳኔ ተግባራዊ አደረገ

አለም አቀፉ የእግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፊፋ ለኢትዮጵያ ቡና የዑጋንዳዊውን ቦገን የ6 ወር ደመወዝ እንዲከፍል የሰጠውን ውሣኔ ተግባራዊ ማድረጉን ኢትዮጲያ ቡና አስታውቋል።

ጋናዊው ተጨዋች ለፊፋ ያቀረበው ክስ ተግባራዊ መሆኑ የግድ ቢሆንም ተጨዋቹ የሄደበት መንገድ ለኢትዮጵያ ቡና ዋና ስራ አስኪያጅ ለአቶ ገዛኸኝ ወልዴ የተዋጠ አልሆነም፡፡ “በፍፁም ተገቢ አካሄድ አይደለም ለዲሲፕሊን ኮሚቴ ሳያሳውቅ በቀጥታ ለፊፋ መክሰሱ ተገቢ አልነበረም፤ ነገር ግን ጉዳዩን ወደ ፊፋ ለመውሰድ የሄድንበት ጊዜ ይግባኝ የማቅረቢያውን ቀነ ገደብ በማለፉ መሸነፋችንና የተባለውን ገንዝብ መክፈላችን የግድ ሆኗል” ሲሉ አቶ ገዛኸኘ ገልፀዋል፡፡

ፊፋ ክለቡ የተጨዋቹን ደመወዝ እስኪከፈል ድረስ በሚል የኢትዮጵያ ቡና የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ተጨዋቾች ዝውውርን በማገድ የቆየ ሲሆን ክለቡ ለተጨዋቹ በውሉ መሠረት ገንዘቡን ከከፈለ በኋላ ግን የዝውውር እገዳው መነሳቱን ሀትሪክ ስፖርት ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.