ቀያይ ሴጣኖቹ ተከታታይ ሽንፈትን አስተናገዱ !
በ ኦሊ ጎነር ሶልሻየር የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል ።
የቱርኩ ሻምፒዮን ኢስታንቡል ባሳክሼር በክለቡ ታሪክ የመጀመሪያ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ድላቸውን ማስመዝገብ ችለዋል ።
በተቃራኒው ደግሞ ትላንት ምሽት በተጠናቀቀው የሶስተኛ ሳምንት መርሀ ግብሮች ጀርመንን ወክለው እየተሳተፉ የሚገኙት ባየር ሙኒክ ፤ ዶርትመንድ ፤ ሌፕዚግ እንዲሁም ሞንችንግላድባህ አራቱም ድል ቀንቷቸዋል ፡፡
በተያያዘም ዛሬ ምሽት በሚካሄደው የዩሮፓ ሊግ መርሐ ግብር 2፡55 ቶተንሀም ከ ሉዶጎሬትስ ፣ ሪያል ሶሴዳድ ከ አልከማር እንዲሁም 5፡00 አርሴናል ከ ሞልድ ፣ ኤሲ ሚላን ከ ሊል ፣ ቪያሪያል ከ ማካቢ ቴል አቪቭ ተጠባቂዎች ናቸው፡፡