Skip to content
የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከመረጣቸው 36 ተጨዋቾች ሽመልስ በቀለን ጨምሮ ከቀሩት 27 የቡድኑ አባላት መካከልበረከት ደስታ አንዱ ሲሆን ነገር ግን ፍቃድ አግኝቶ ወጥቶ እያለ በተፈቀደለት ጊዜ ባለመመለሱ ምክንያት ከቡድኑ ሊሰረዝ መቻሉ ታውቁአል

ከ27 ተጨዋቾች 4ቱ የሚቀነሱ በመሆኑ በረከት ከተቀናሾቹ መሃል ይሁን አይሁን የታወቀ ነገር አልነበረም ትልቅ አገራዊ አጀንዳ ላይ የተጠራው ተጨዋቹ ግን ከሰአታት በፊት በደረሰኝ መረጃ በሰርግ ምክንያት ከካፍ አካዳሚ ከሚገኙት ተጨዋቾች ውጪ ሆኗል፡፡
መጀመሪያውኑ የተቀነሱት ተጨዋቾች ዝርዝር ከመታወቁ በፊት ተናግሮ ቢሆን ኖሮ በሱ ቦታ ከተቀነሱት ተጨዋቾች አንዱ ይቀር ነበር በማለት የበረከትን ድርጊት የስፖርት ቤተሰቡ ተችቷል፡፡ ቡድኑ ህዳር 4 ኒጀርን ገጥሞ የሚመለሰው ህዳር 6 ሲሆን ይህም ቀን የበረከት የሰርጉ ቀን መሆኑ ታውቋል፡፡
ከታማኝ ምንጭ በተገኘ ሌላ የበረከት መረጃ ሰኞ ዕለት ወደ አዳማ ሄዶ ማክሰኞ ምሽት 12 ሰአት ለመመለስ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ፍቃድ አግኝቶ ከአካዳሚው ከወጣ በኋላ በተባለው ሰአት ባለመመለሱ አሰልጣኙ ደጋግሞ በእጅ ስልኩ ላይ ቢደውልም በረከት ምላሽ አለመስጠቱ አሰልጣኙን አበሳጭቷል፡፡
ተጨዋቹ ዛሬ ጠዋት ሲደውል በአሰልጣኙ መመለስ እንደማይችል መቀነሱ እንደተነገረውና በዚህ የዲሲፕሊን ጥሰትም ከቡድኑ መባረሩ ታውቋል፡፡
ምናልባት ሲደወልለት ያላነሳው ከ27ቱ ቀሪ ተጨዋቾች መሃል እሆናለሁ የሚል እምነትም ስላልነበረው ይሆናል የሚልም ግምት አለ፡፡ ዋሊያዎቹ በቀናቶች ውስጥ ደግሞ ቀሪዎቹ አንድ ግብ ጠባቂና ሁለት ተጨዋቾች ቀንሰው ጠንካራ ልምምዳቸውን ይቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል ስትል ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ዘግባለች፡፡