“ይህ ለሊቨርፑል ነው”
አንድሪው ሮበርትሰን ( ግንቦት 29 2019 እ.ኤ.አ.)
(ክፍል ሶስት)
ሰዎች ለሊቨርፑል የመጫወትን ጫና ሁል ጊዜ ይጠይቁኛል ፡፡ ያ እዚያ አለ፣ እመኑኝ ፣ ይሰማኛል ፡፡ ግን ያ ጫና አለ እና እንዲሁም የህይወት ጫና በራሱ አለ – ማወቅ ያለብን ነገር ይህንን ጫና መቋቋም ካልቻሉ የሚወዱትን ነገር ሁሉ የማጣት እድል እንዳለ ነው፡፡ ያ ጊዜ ተሰምቶኝ የማያውቀው ከፍተኛ ጫና ያለበት ወቅት ነበር። እናም በእዚያ ሁኔታ ውስጥ ፣ በራሴ በእውነት ማመን ጀመርኩ – ምናልባትም በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ፡፡ በእውነቱ ሌላ ምርጫ አልነበረኝም።
ደንዲይ ዩናይትድ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ወደ እኔ ቀረበኝ ፣ እናም ይህ በየቀኑ ስልጠና እንዳገኝ እና በቂ ገንዘብ እንዳገኝ አስችሎኛል። ይህ ነገር ግን ከእግር ኳስ ሰዎች ከእለት ተእለት የሚያደርጓቸውን ነገሮች ለማየት ጥሩ አጋጣሚ የሆነኝ ይመስለኛል ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2014 በፕሪሚየር ሊጉ ከሁል ሲቲ ጋር በፕሪሚየር ሊግ የመጫወት እድል ባገኘሁ ጊዜ ብዙ እውነተኛ ህይወት አጋጣሚዎችን መኖር ጀምሬያለው፡፡ ምኞቶቼ ሁልጊዜ ጠንካራ የስኮትላንድ ሊግ ተጫዋች መሆን ነበር። ቦታዎችን በማስተካክልበት እና የቆሻሻ ቅርጫቶችን በምሰበስብበት ጊዜ ፣ በሻምፒዮንስ ሊግ የምጫወት አይመስለኝም ነበር በተለይም ለሊቨርፑል፡፡
አስቂኝ ነው ፣ በእውነቱ… እ.ኤ.አ. በ 2017 ከሁል ጋር የቅድመ ውድድር ዝግጅት ጊዜ በነበረበት ወቅት ጥቂት ክለቦች እየፈለጉኝ ነበር፣ ግን በእውነቱ ፍላጎት አልነበረኝም ፡፡ ሚስቴ ነፍሰ ጡር ነበረች ፣ እናም በትልቁ ለሚመጣው ልጅ ሁሉንም ነገር በማዘጋጀት ሂደት ላይ ነበርን፤ እንደማንኛውም ወላጅ ያ የእኛ የመጀመሪያ ደረጃ ጉዳይ ነበርው ፡፡
ከዚያ ሊቨርፑል እንደሚፈልገኝ ሰማሁ ፡፡
ሊቨርፑል!
ሊቨርፑል እርስዎን እንደሚፈልግዎ ሲሰሙ በአምስት ሰከንዶች ውስጥ ወኪልዎ ጋር መደወልዎ አይቀርም፡፡ እውነቱን ለመናገር ውሉን በፍጥነት መፈረም አልቻልኩም ፡፡
ቢሆንም ሁሉንም ተጨባጭ መረጃዎች በፍጥነት አገኘሁ። የሕክምና ምርመራው ለሁለት ቀናት የወሰደ ሲሆን በጭካኔ የተሞላ ነበር ፡፡ የአካል ብቃቴ ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ እና በብቃቴ መቆየቴን ለማረጋገጥ የህክምና ባልደረቦች ብዙ ምርመራዎችን ማድረግ ስላለባቸው የእኔ አመጋገብ ያልተለመደ ሆኖ ነበር። እነዛን ፈተናዎች/ምርመራዎች ካለፍኩ በኋላ የላክቴት(በደም ውስጥ የሚገኝ የላክቴት አሲድ ለማወቅ የሚደረግ ነው) ምርመራ ለማድረግ ወደ ሜልዉድ( የሊቨርፑል የልምምድ ሜዳ) መሄድ ነበረብኝ ፡፡ እኔ ከዳኒ ኢንግ ጋር እሮጥ ነበር፤ በሜዳው ዙሪያ ጥቂት ከዞርን በኋላ ሆዴ ላይ አንድ ነገር ተሰማኝ ፡፡ ነገሮች መጥፎ እንደሚሆኑ አውቅ ነበር ፣ ግን ምን ማድረግ እችለለሁ? መሮጥ ቀጠልኩ ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በጉልበቴ ተንበርክኬ በሜልውድ ሜዳ ላይ የጨነቀኝ ነገርን አስወጣሁት፡፡
ይህ የተቀደሰ መሬት ፡፡ እነዚያ ሁሉ ታላላቅ ተጫዋቾች የሠለጠኑበት ቦታ። ኪንግ ኬኒ፣ ራሽ፣ ስቲቪ ጄራርድ። እና ይኸው ያ ግላስኮ ትንሽ ልጅ በሊቨርፑል የሕክምና ባልደረቦች ፊት አስመለሰኝ፡፡
የመጀመሪያዎቹ ትዕይንቶች ቢቆጠሩ ፣ እግዚአብሔር ስለ እኔ ምን እንዳሰቡ ያውቃል ፡፡
በሚቀጥለው ቀን አሰልጣኙን በአንድ ማይል ርቆ ሲስቅ ሰማሁት፡፡ ዞር አልኩ፣ ወደ እኔ እየመጣ በአንድ እጁ ሆዱን ይዞ በሌላኛው ወደ እኔ እየጠቆመ ነበር። ከጀርባው ያሉት ባልደረቦቹም እንዲሁ እየሳቁ ናቸው፡፡ በትክክልም ስለ ምርመሪያዬ በሙሉ ሰምቷል፡፡
ከዚያ በደንብ እቅፍ አደረገኝ፡፡ ከዚያ በኋላ ትንሽ ዘና አልኩ፡፡
መላው ቡድኑ በዚያ ሳምንት ጥሩ አቀባበል አድርጎልኛል ፣ ግን እውነቱን ለመናገር እኔ እንደ ሊቨርፑል ተጫዋች በዚያ ሙድ ውስጥ ለመግባት በእውነት ረጅም ጊዜ ፈጅቶብኛል ፡፡ ቀዩን ሸሚዝ እለብስ ነበር ፡፡ ወደምንሄድበት ቦታ ሁሉ የክለቡን ቱታ እለብስ ነበር ፡፡ ቤቴም እለብሰው ነበር ፡፡ ግን አሁንም እንደ ሊቨርፑል ተጫዋች አልተሰማኝም ነበር፡፡
እኔ ለተወሰኑ ወራት በመጀመሪያው አሰላለፍ ወጣ ገባ እል ነበር፡፡ እኛ የምንጫወትበት ስርዓት በጣም የተወሳሰበ ነው ፣ ሁሉንም ለመማር በስልጠናው ጠንክሬ እየሰራሁ ነበር በተለይ አሰልጣኙ ከመስመር ተከላካዮች ምን እንደሚፈልግ ለማወቅ እጥር ነበር፡፡ በጨዋታ እለት በቡድን አሰላለፍ የሚያሳየው ወረቀት ላይ ስሜን ሳላየው ስቀር፣ በራሴ ላይ ያለኝ እምነት መቀነስ ጀመረ ፡፡ ግን በህይወቴ ውስጥ ያጋጠሙኝ ልምዶች ሁሉ እና በሴልቲክ እና በኩዊንስ ፓርክ ውስጥ ያለፍኩባቸው አስቸጋሪ ጊዜያት ሁሉ ታጋሽ መሆንን አስተምሮኛል ፡፡
ስለዚህ በየቀኑ ወደ ስልጠና እመጣለው እናም ጠንክሬ በመስራት የአሰልጣኙን እይታ ለማግኘት እሞክራለሁ። በመጨረሻ አስተዋልኩ፤ እሱ በራስ የመተማመን ስሜቴ እንዲያድግ እና የሊቨርፑል ተጫዋች መሆኖ እንዲሰማኝ እና እሱ እስኪገባኝ ድረስ እየጠበቀኝ እንደሆነ ተገነዘብኩ፡፡ በመጨረሻም ወደ አሰላለፍ ስገባም፣ ዝግጁ ነበርኩ ፡፡
እዚህ ከገባሁበት ጊዜ ጀምሮ ደጋፊዎቼ ለእኔ አስገራሚ ነበሩ ፡፡ እና ባለፈው ዓመት እነሱ እስከ መጨረሻው ፊሽካ እንዲሁም ከዚያም በኋላ እስከ ኪየቭ ድረስ ሙሉ በሙሉ እየደገፉን ከጎናችን ነበሩ። ያ ምሽት ከባድ ነበር ፣ እና በእውነቱ እንደዚህ የመሰለ ግጥሚያ መቼም የሚገኝም አይመስለኝም። እርስዎ ብቻ እያስታወሱት ይኖራሉ። ያን ምሽት በመልበሻ ክፍላችን ውስጥ ያለውን ዝምታ አስታውሳለሁ፣ ወደሊቨርፑል ለመመለስ ባደረግነው በረራ የነበረውን የጥልቅ ሀዘን ስሜት አስታውሳለሁ። እና ከመጨረሻው የፊሽካ ድምጽ በኋላም “መቼም ብቻችሁን አይደላችሁም”(“You’ll Never Walk Alone”) የሚለውን የደጋፊዎቻችን ዜማ መስማቴን አስታውሳለሁ።
ደጋፊዎቹ አሁንም ከልባቸውን ዘፈኑ ፣ ያ ካንተም ጋር አብሮ ይቆያል ፡፡
በማለዳ አራት ሰዓት ላይ ወደ ሜልዉድ( የሊቨርፑል የልምምድ ሜዳ) ተመለስን ፡፡ አሰላጣኛችንም ሁላችንንም እቅፍ እያደረገ በቡድናችን ምን ያህል ኩራት እንደሚሰማው ነግሮናል ፡፡ ተመልሰን እንደምናደርገውም ነግሮናል ፡፡ የሆነ ሆኖ በጣም ከረጅም መንገድ በኋላ… በባርሴሎና የ3-0 ወኔ አፍሳሽ ሽንፈትም በኋላ… እሱ ትክክል ነበር ፡፡
ተመልሰናል!
ይህ አጋጣሚ ምን ማለት እንደሆነ ለሁላችንም አይጠፋንም። ይህ እጅግ በጣም ብዙ እና ውጣ ውረድ እና ስሜታዊ ጊዜያት የሞላበት አስደናቂ የውድድር ዘመን ነበር ፡፡ ለእኔ ግን አንድ እርምጃ ወደ ኋላ በመመለስ እና ሙሉውን የህይወቴን ስዕል ለማየት እድሉንም የሰጠኝ ነበር፡፡ በሴልቲክ አትፈለግም ተብሎ መለቀቅ ጀምሮ እስከ ስድስት ፓውንድ ለማግኘት ከስኮትላንድ እርቆ መሄድ፣ ለሊቨርፑል መፈረም እና ያንን ቀይ ቱታ መልበስ ፣ ማመን ነው ፡፡
በመጨረሻው ሌላ የፍፃሜ እድል ጥሩ ስሜት አለው፡፡ በመልካም ጊዜያት እና በሀዘኑ ወቅት ድጋፍ ከሰጡን ደጋፊዎቻችን የበለጠ ይህ የሚገባው ማንም የለም ፡፡ ግን እንደ እኛ እነሱም በስፐርስ ላይ የበላይ መሆናችንን ያውቃሉ ፡፡ ሞውሪዚዮ ፖቼቲኖ እና ተጫዋቾቹ በመጨረሻው ጨዋታ አንድ ለየት ያለ ነገር ለማድረግ እንደምንሞክር አስበው ይዘጋጃሉ፡፡
በጣም አስፈላጊው ነገር እጣ ፈንታችን በእጃችን ውስጥ መሆኑ ነው። እኛ እናውቃለን። እናም ስለዚህ ቡድን ፣ ስለነዚህ የተጫዋቾች ስብስብም የማረጋግጠው አንድ ነገር ካለ የአድናቂዎቻችንን ህልም እውን ለማድረግ ምንም ዓይነት የማናደርገው ነገር የለም፡፡
ያ ካልሆነ እውነተኛ አፈታሪክ (ተረት ተረት) አይሆንም።
ምክንያቱም፤እኛ ይገባናል!
አንድሪው ሮበርትሰን ( ግንቦት 29 2019 እ.ኤ.አ.)
ሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ