“ይህ ለሊቨርፑል ነው”
አንድሪው ሮበርትሰን ( ግንቦት 29 2019 እ.ኤ.አ.)
(ክፍል ሁለት)
ኦ በቃ አላምንም ! አውቅ ነበር፣ ምን እንደሚመጣ አውቅ ነበር፤ በአንፊልድ ምን እንደሚፈጥር ፡፡ በምንም መንገድ የንቀት ንግግር ነው ብላችሁ እንደማትመለከቱት ተስፋ አደርጋለሁ እኔ ለባርሴሎና የበለጠ አክብሮት ግን አልነበረኝም ፤ ነገሩ በዚያን ምሽት ስለእነሱ አልነበረም ፡፡ ስለ እኛ ነበር ፡፡ በአድናቂዎቻችን አስደናቂ ድባብ የድል ረሃባችን በሌላ ደረጃ ላይ ነበር ፡፡
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ሜሲ እንደዚያ አይነት አስማት ካሳየን በኋላ እንደዚህ እንደዚያ ዓይነት ስሜት ሊሰማኝ ይችላል ብሎ ለማመን በጣም ከባድ ነበር፡፡በዚያ ጊዜ እምነታችን ተሸርሽሮ ነበር፤ ምናልባትም የማይቻል ነበር ፡፡ እኛ በባርሴሎና የነበረን ቢሆንም ማድሪድ ሩቅ እንደሆነች አይሰማንም ነበር፡፡ ከዚያ አሰልጣኛችን ያ መገለጫው የሆነውን ፈገግታ እንደተላበሰ ወደ መልበሻ ክፍል መጣ፡፡
“ልጆች፣ ልጆች፣ ልጆች!” አለን፣ “እኛ አሁን በዓለም ላይ ያለነው ምርጡ ቡድን አይደለንም ፡፡ አሁን ያንን አውቃችኋል፡፡ ምናልባት እነሱ ሊሆኑ ይችላሉ! እኛ ምን አገባን? ማን ምንአገባው! አሁንም በዓለም ውስጥ ያለውን ምርጡን ቡድን ማሸነፍ እንችላለን ፡፡ እንደገና እንሂድ እንሞክር፡፡”
እሱን ለማመን ሰከንዶች ሊወስድብኝ ይችላል ፣ ወይም ምናልባትም ወደ ሊቨርፑል የምንመለስበት ሙሉ በረራም ያህልም ማሰብ እሱን ለማመን ፈጅቶ ይሆናል፤ ነገር ግን ወደ ኋላ መለስ ብለን ስናስብ ሁሉንም ነገር የቀየረው አጋጣሚ ለኛ ያ ነበር ፡፡ በእግር ኳስ ውስጥ ሁሉም ሰው ሁል ጊዜ ስለ እምነት ይናገራል ፡፡ እያንዳንዱ ቡድን ያንን በድጋሚ ተመልሶ ማሸነፍን ከቻሉ በኋላ በእምነታቸው እንዳገኙት ይናገራሉ። ነገር ግን በእያንዳንዱ ክበብ ውስጥ ጉዳዩ እንደዚያ አይደለም ፡፡ ልክ አይደለም። ለኛ አሰልጣኙ፣ እሱ ሁሉንም ጀምሮታል፡፡ እሱ ጭላንጭል ብርሀኑን አብርቶልናል፣ ከዚያም አንፊልድ የሚሠራውን ሰርቷል፡፡
አስታውሳለሁ በምናሟሙቅበት ወቅት ስታዲየሙ እየተናወጠ ነበር። ሁሉም ከእኛ በላይ እንዳመኑ ያስታውቃል፣ እግዚአብሔር ይወቀው ለባርሴሎናውያን ተጫዋቾች ሁኔታው ምን እንደሚመስል፡፡ኦሪጊ በጊዜ ግቡን ሲያስቆጥር፣ በዓይኖቻቸው ውስጥ ብቻ ያንን ማየት ይችላሉ ፡፡ አድናቂዎቹ እብድ ሆኑ ፡፡ አንድም ነገር ግን ግልፅ ብሎ መስማት አልቻልኩም። ሄንዶ ፣ ሚሊ እና ቨርጂልን መመልከቴን በቃ ትዝ ይለኛል – እነዚያ ሰዎች ፈገግታ የላቸውም ፡፡
እጆቻቸውን ብቻ ለደጋፊው እያወዛወዙ “ እንደገና እናደርገዋለን!” የሚሉ ይመስላሉ ፡፡
ያ ምሽት በታሪክ ውስጥ ይመዘገባል ብዬ እገምታለሁ ፡፡ ይህንን ክበብ የሚወድ ማንኛውም ሰው በዚያን ቀን የት እንደነበሩ እና ከማን ጋር እንደነበሩ ያስታውሳሉ። ለእኔ በግሌ ፣ የበለጠ ልዩ ያደረገው ትልቁ ነገር እዚያ ለመድረስ የመጣሁበት መንገድ ነው፡፡
አውቃለው! ምን ያህል ከባድ እንደሆነ አስታውሳለው፣አውቃለው ሌሎችን ባዳምጥ ኖሮ በዚህኛው ምሽት ምናልባት ድባቡ ምን እንደሚመስል ለመመልከት ከሚፈልጉ አድናቂዎች አንዱ ሆኖ ከመገኘት በስተቀር ወደ አንፊልድ አቅራቢያ የምቀርብበት ምክንያት አይኖርም ነበር፡፡
ከእናቴ፣ ከአባቴና ከወንድሜ ጋር ወደ ሴልቲክ ፓርክ ሄጄ ነበር ፡፡ የአራት የውድድር ዘመን ቲኬቶች ነበሩን ፡፡ እኔና ወንድሜ የሄንሪክ ላርሰን ፖስተሮች በሁሉም ቦታዎቻችን ላይ ነበረን፡፡ ታላቅ የእውነት ታላቅ ባለታሪክ ፡፡ እኔ የቤቴ የግድግዳ ወረቀት ጭምር አረንጓዴ ነበር፡፡ ሴልቲክ የቤተሰባችን አንድ አካል ነበር። ያ ነበር በትክክል እና አሁንም እንደዛው ነው ፡፡ ህፃን/ታዳጊ እያለው በሴልቲክ ታዳጊ ቡድን ውስጥ እንደገባው በሜዳው ዳር ሆኜ ልክ በሴልቲክ ፓርክ ውስጥ የገባው ይመስል ፈነጠዝኩ ፡፡
መጀመሪያ ላይ ለተወሰነ ጊዜ በፊት መስመር ላይ ነው ተጫወትኩኝ ፡፡ ሌላው ቀርቶ አባዬ ሁለት ኳይድ(ፓውንድ) ጎል ባገባው ቁጥር ይሰጠኝ ነበር፡፡ እናም በአንድ የውድድር ዘመን 75 ፓውንድ ያገኘሁ ይመስለኛል፡፡ እስከ አሁን በዛው ብቀጥል ኖሮ የሱንም ገንዘብ መውሰዴ ያበቃላት ነበር እንዲሁም እንደ ሳላህ አይነት ጎል አስቀጣሪ መሆኔም ያጠራጥረኛል፡፡ከጊዜ በኋላ ቦታዬ ወደ መሀል ሜዳ ተጫዋችነት ተቀየረ፡፡በመጨረሻው ከሴልቲክ ጋር በቆየሁበት የውድድር ዘመን በመሃል ሜዳ እና በግራ ክንፍ በኩል በመጫወት አሳልፊያለው፡፡ በዚያ ዓመት ሴልቲኮች አዲስ የቴክኒክ ዳይሬክተር ይቀጥራሉ እናም በምንም ምክንያት ሊሆን ይችላል ብቻ የእቅዳቸው አካል አልሆንኩም።
በአመቱ መጨረሻ ላይ አሰልጣኞቹ በቀጣዩ የውድድር ዘመን መልሰው እንደማይመልሱኝ/ እንደማያጫውቱኝ ከውድደሩ መጠናቀቅ በኋላ አሳውቀውኛል ፡፡ አስራ አምስት አመቴ ነበር ፡፡ ለዋናው የሴልቲክ ቡድን ለመጫወት አንድ አመት ሲቀረኝ። ግን አበቃ፣ ልክ እንደቀላል ፣ እናም ገሃነም እንደገባ ሰው ሆንኩ፤ በጣም ተጎዳሁ ፡፡
እማዬ እኛ ልጆቿ ስናለቅስ ማየት ትጠላለች፤ አሁንም ቢሆን፡፡ ግን ያን ቀን እያነባው አየችኝ ፡፡ አስታውሳለሁ እኔን ለማፅናናት ብላ ከምወደው የሰፈሬ ኩሬ ይዛኝ ሄደች፡፡ የሳምንቱ አጋማሽ ላይ ነበር ፡፡ እኔ በየሳምንቱ መውሰድ የነበረብኝን የተመጠነ ምግብ እንኳን በፍፁም አልወሰድኩም ነበር፡፡ ያንን እንኳን መመገብ አልቻልኩም ነበር። ለዚያም ነበር ምን ያህል በእጅጉ እንደተጎዳሁ የተረዳሁት።
በቃ የመያበሳጭ ነበር፣ ግን ደግነቱ ቤተሰቤ በእውነቱ ከጎኔ ነበሩ፡፡ ሁኔታው ለመቀጠል የሚበረታታ ባይመስልም እንኳ ሕልሜን ለማሳካት በማደርገው ጥረት ያግዙኝ/ይደግፉኝ ነበር። እ.ኤ.አ. በ 20100 ኩዊንስ ፓርክ እኔ እንድቀላቀል ወሰንን ፡፡ በግላስኮ የሚገኘው ትንሽ ክለብ፡፡ በትንሹ ማለት የሚቻለው በእዚያም ሕይወት ትንሽ ከባድ ነበር ፡፡ በአንድ ሌሊት ስድስት ፓውንድ እሠራ ነበር ፡፡ ክለቡ ከሰራተኛው መደብ የሚመደብ ነበር፤ አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች የሚመጡት በቀን ውስጥ ከሚሰሯቸው ስራዎች ነው። ለእኔም የተለየ አልነበረም ፡፡
ከትንንሽ ስራዎች ጀምሮ ሁሉንም ዓይነት ስራዎችን ሠርቻለሁ ፡፡ ሜዳ/መሬት አቀማመጥ ከማስተካከል ጀምሮ፣ ከመጀመሪያው ቡድን ጨዋታ በኋላ ስታዲየም አፅድቻለሁ እና በስኮትላንድ ግጥሚያዎች ወቅት ሃምፔደን ፓርክ ውስጥ እንኳ እሠራ ነበር ፡፡ በዚያ ዓመት የመጫወት እድል የማላገኝ ከሆነ ሌሎች አማራጮችን ምርጫዎች መመልከቱ ምናልባት የተሻለ ሊሆን እንደሚችል ወላጆቼ ነግረውኛል፡፡ ስለዚህ ወደ ተሻለ ደረጃ ያለኝን ሁሉ በየቀኑ ማስቀመጥ ነበረብኝ ፡፡ ያ እውነተኛ ሥራ ፣ እውነተኛ ጫና ነበር ፡፡
(ይቀጥላል…)