በዚህ ሳምንት የነበሩ የሀገር ውስጥ የዝውውር መረጃዎች
ሀዲያ ሆሳዕና
ከቀናት በፊት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን ወደ ዋና አሰልጣኝነት የቀጠሩት ነብሮቹ 3 የአዳማ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል እነዚህም
አዲስ ህንጻ (ኢትዮጵያ መድህን ፣ ንግድ ባንክ ፣ ደደቢት እና የሱዳኑ ሒላል ሸንዲ እንዲሁም አዳማ ከተማ መጫወቱ ይታወቃል)
ቴዎድሮስ በቀለ (መከላከያ እና አዳማ መጫወቱ ይታወቃል) {ሁለገብ ተከላካይ}
በረከት ደስታ (ከአዳማ ሁለተኛ ቡድን አደገ ከዛ እዛው አዳማ ከተማ መጫወት ጀመረ{የመስመር ተጫዋች}
ድሬዳዋ ከተማ
ሱራፌል ጌታቸውን አስፈርሟል (ሙገር ሲሚንቶ፣ ለአዲስ አበባ ከተማ፣ ለጅማ አባቡና፣ ለአዳማ ከተማ እና ለሀድያ ሆሳህና መጫወቱ ይታወቃል{ በአጥቂ አማካይ}
ወልቂጤ
ከቅዱስ ጊዮርጊስ አቡበከር ሳኒን ያስፈረሙት ክትፎዎቹ በሊጉ ልምድ አላቸው ተብሎ ከሚጠሩት የአማካይ ስፍራ አንዱ የሆነውን ፍሬው ሰለሞንን[ጣቁሩ] ከመከላከያ ማስፈረማቸው ይፋ ሆኗል ።{መከላከያ ፣ ሐዋሳ ከተማ እና ሙገር ሲሚንቶ መጫወቱ ይታወቃል}
ባህርዳር ከነማ
በአዳማ ከተማ ቤት ያለፉትን ዓመታት ማሳለፍ የቻለው የመሀል ተከላካዩ መናፍ ዓወል የጣና ሞገዶቹን የተቀላቀለ ሌላኛው ተጫዋች ሆኗል ።
ሌላኛው ተጫዋች ደግሞ ያለፉትን በርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ቡና ቤት ማሳለፍ የቻለው አህመድ ረሺድ የጣና ሞገዶቹን ለመቀላቀል ተስማምቷል ።
