አትሌቶቹ በቻርተርድ አውሮፕላን ተጉዘው በጀርመን ግብዣ ተደረገላቸው!

ባሳለፍነው እሁድ በለንደን ማራቶን ከ2 ሰአት በታች በመግባት ታሪክ የሰሩት ሳዌ እና ዮሚፍ የአዲዳስ አትሌቶች ሲሆን  በራሷ ተይዞ የነበረውን የሴቶች ብቻ ሪኮርድን ያሻሸለችው ትግስት አሰፋም እንዲሁ የተቋሙ አትሌት እንደሆነች ይታወቃል። አዲዳስም ታዲያ እኚህ ጀግና አትሌቶቹን ከለንደን ወደ ጀርመን በ’ቻርተርድ’ አውሮፕላን ወስዶ ልዩ ግብዣ አድርጎላቸዋል።

አሁን ላይ በአትሌቶች የማራቶን አሸናፊነት ጀርባ ከአትሌቶቹ ባልተናነሰ ብርቱ ፉክክር ላይ የሚገኙት ናይክ እና አዲዳስ ሲሆኑ ናይክ ልዩ ፕሮጀክት በመቅረፅ ለኤሉድ ኪፕቾጌ ሁሉንም ምቹ ሁኔታዎች በማመቻቸት ከ2 ሰአት በታች እንዲገባ ‘ ኢንዮስ 1:59’ የተሰኘ ቻሌንጅ ሰጥቶት እንደተወጣው ይታወሳል። ይሁንና በሰአቱ የታዩት ቴክኖሎጂዎች ይፋዊ የተመዘገበ ውድድር እንዳይሆን አድርጎታል። አዲዳስ ታዲያ በይፋዊ ውድድር ሊያውም ደግሞ የፕላቲንየም ደረጃ በሚሰጠው የለንደን ማራቶን ይሄን ማሳካቱ ተከትሎ የአድናቆት ቸሮታዎች እየጎረፉለት ይገኛሉ።

✍️ ዮናታን አየለ

Leave a Reply

Your email address will not be published.