4ኛው ኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ሚያዝያ 18/ 2018 ዓ.ም ይካሄዳል!
4ኛው የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ ሚያዝያ 18/2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን በጋራ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። በዚህ ውድድር ከክለቦች እና ተቋማት የተውጣጡ ከ500 በላይ አትሌቶች ተሳታፊ እንደሚኾኑም ይጠበቃል።ይህ ውድድር የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ችግሮች ለመፍታት እና ዘርፉን ለማሳደግ የተጀመረውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለማስተዋወቅ የጎላ ሚና እንደሚኖረው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል።

የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አስተባባሪ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ሩጫው የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማስተዋወቅ እና የማምረት አቅማቸውን የማሳየት ዕድል ይፈጥራል ብለዋል። ጤናማ ፣ አምራች ዜጋን የመፍጠር እና ዕድል ላላገኙ አትሌቶች የውድድር ዕድል የመፍጠር ዓላማ እንዳለውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የውድድርና ተሳትፎ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ጊዜ አድነው የኢንደስትሪ ሚኒስቴር በየዓመቱ የሚያካሂደው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ውድድር ለአትሌቲክስ ስፖርት ልማት ከፍተኛ ሚና ያለው መኾኑን ተናግረዋል። ይህ ውድድር በስኬት እንዲካሄድ ፌዴሬሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል ብለዋል።ይህ ውድድር በቀጣይ እያደገ እንዲሄድ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ጭምር ታዋቂ እንዲኾን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የበኩሉን እንደሚወጣ ተናግረዋል።
በዚህ ውድድር ከ1 እስከ 10 ለሚወጡ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከት ተገልጿል:-
1ኛ ለሚወጡ 550 ሺ ብር
2ኛ ለሚወጡ 300 ሺ ብር
3ኛ ለሚወጡ 200 ሺ ብር
4ኛ ለሚወጡ 150 ሺ ብር
5ኛ ለሚወጡ 100 ሺ ብር ሽልማት ይበረከታል።
via EthiopianAthleticsFederation
✍️ ዮናታን አየለ
