ድርቤ ወልተጂ የሁለት አመት እግድ ተጣለባት!
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድርቤ ወልተጂ በስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት የ2 አመት ቅጣት እንደተጣለባት ” Athletics Integirty Unit” ይፋ አድርጓል። አትሌቷ ባሳለፍነው አመት ወርሀ የካቲት 2017 ላይ ከውድድር ውጭ የሆነ ድንገተኛ የዶፒንግ ምርመራ እንዲደረግላት ናሙና ስትጠየቅ ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነችም ተብሎ በኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ሪፖርት መደረጉ የሚዘነጋ አይደለም።
የፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲው የቶክዮ አለም ሻምፒዮና ሊጀምር ጥቂት ቀናት ሲቀሩት በወርሀ ነሀሴ አትሌቷን በነፃ ቢያሰናብትም የአለም አትሌቲክስ ግን ጉዳዩን ወደ አለም አቀፉ የስፖርት ግልግል ፍርድቤት( CAS) ከወሰደ በኋላ ከቶክዮ የአለም ሻምፒዮና አግዷት ነበር።
የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔም ትላንት የታወቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ምንም እንኳን አትሌቷ ሆን ብላ ያላደረገችው ነገር እንደሆነ ማመኑን ጠቅሶ ይሄ ግን ከቅጣት እንደማያድናት እና ምርመራውን በዛን ወቅት ለምን እንዳላደረገች የሚገልፅ አሳማኝ ምክንያትም ባለመቅረቡ ለእግዱ ምክንያት እንደሆነ ገልጿል።
ድርቤ በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በናንጂንግ ያገኘችውን የብር ሜዳሊያ ጨምሮ እ.ኤ.አ የካቲት 25,2026 በኋላ ያስመዘገበችው ውጤት በሙሉ የሚሰረዝ ይሆናል።
