አርጀቲና ሜክሲኮን አሸነፈች

አርጀቲና  ሜክሲኮን አሸነፈች

የኳታር 2022 የፊፋ የአለም ዋንጫ የምድብ 3 ሁለተኛ ዙር ጨዋታ ቅዳሜ ህዳር 17 ቀን 2015
ምሽት 4 ሰአት በተደረገ ጨዋታ
አርጀቲና ሜክሲኮን በሜሲና በፈርናንዴዝ ጎሎች 2ለ0 አሸነፈች።

አርጀንቲና 2-0 ሜክሲኮ
⚽️ሜሲ 64′
⚽️ፈርናንዴዝ 84′

በምድቡ መጀመሪያ ጨዋታ  ሳውዲ አረቢያ አርጀንቲናን 2 ለ 1 ስታሸንፍ ፖላንድና ሜክሲኮ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል ።
ዛሬ ቀን  10 ሰአት ላይ ደግሞ በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ፖላንድ ሳውድአረቢያን 2 ለ0 አሸንፋለች

በዚህ መሠረት
👉ፖላንድ በ4 ነጥብና 2 ንጹህ ጎል አንደኛ

👉አርጀንቲና በ3 ነጥብና በ1 ንጹህ ጎል ሁለተኛ ።
👉ሳውዲ አረብያ በ3 ነጥብና በ1 የግብ እዳ ሶስተኛ
👉ሜክሲኮን በ1 ነጥብ በ2 የግብ እዳ አራተኛ ላይ ተቀምጠዋል።

በቀጣይ የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ህዳር 21 ቀን 2015  አ/ም

👉 ፖላንድ ከአርጀንቲና

👉ሳውድአረቢያ ከሜክሲኮ የሚጋጠሙ ይሆናል ።

👉በዛሬው ጨዋታ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ ስምንት ማድረስ ችሏል በዚች ጎል ምክኒያት የዲያጎ ማራዶናን የ8 ጎል ታሪክ ተጋርቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.