ትዕይንታዊ ክስተቶች የታዩበት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች።
▪️የአውሮፖ ሻምፒዮንስ ሊግ 3ኛ ሳምንት የምድብ ጨዋታዎች በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ተካሂደው ነበር።
ምድብ 5 ላይ በሜዳው ያደረጋቸውን ያለፉትን 3 የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለው የካታሎኑ ቡድን ባርሴሎና ዳይናሞ ኪዬቭን በካምፕ ኑ አስተናግዶ በጄራርድ ፒኬ የ36 ደቂቃ ብቸኛ ግብ 1-0 አሸንፏል።ጄራርድ ፒኬ 16ኛ የሻምፒዮንስ ሊግ ጎሉን ሲያስቆጥር ከ ሮቤርቶ ካርሎስ ጋር እኩል ጎል ያስቆጠረ ተከላካይ ያደርገዋል።
በዚሁ ምድብ የፖርቹጋሉ ቤኔፊካ የጀርመኑን ሀያል ክለብ ባየርሙኒክን በ ስታዲዮ ዳሉዝ አስተናግዶ 4-0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።በ ሁለቱም ቡድኖች ጥሩ እንቅስቃሴ የታየበት ሲሆን በሙከራ ደረጃ ባየርሙኒክ ሀይለው አምሽተዋል የመጨረሻዎቹን 20 ደቂቃዎች መቋቋም ያቃታቸው የሆርጌ ጂሰስ ልጆች በ ሊሮይ ሳኔ አስደናቂ ቅጣት ምት ግብ መሪ ሲሆኑ በቤኔፊካ በኩል አጥቂውን ያሬምቹክ ቀይሮ የገባው ኤቨርተን ራሱ ላይ ጎል አስቆጥሮ ልዩነቱን ወደ 2 አስፍቷል። ሌዋንዶስኪ እንዲሁም ሳኔ አከታትለው ባስቆጠሯቸው ጎሎች ባየር ሙኒክ ሙሉ 3 ነጥብ ይዞ ተመልሷል።
ምድብ 6 የኢንግሊዙ ማንቸስተር ዩናይትድ የጣልያኑን አታላንታ በ አሸልድ ትራፎርድ አስተናግዶ 3-2 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ጫና ውስጥ የነበረው እና 2-0 እየተመራ የ እረፍት ወደ መልበሻ ክፍል ያመራው የ አሸሌ ጎነር ሶልሼሩ ማን ዩናይትድ ከ እረፍት መልስ በ ማርከስ ራሽፈርድ ፣ ሀሪ ማጎየር እንዲሁም መደበኛው 90 ደቂቃ ሊጠናቀቅ 9 ደቂቃ ሲቀረው ፖርቹጋላዊው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ቡድኑ ሙሉ 3ነጥብ እንዲያገኙ ያስቻለች ግብ ከመረብ አገናኝቷል።ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ለ2ተኛ ጊዜ በ 3 ተከታታይ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ጎል አስቆጥሯል።እ.ኤ.አ በ 2007 ህዳር ወር ላይ ሻምፒዮንስ ሊጉን ከ ማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ሲያነሳ እንዲሁ በ 3ተከታታይ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ጎል አስቆጥሮ ነበር።ማንቸስተር ዩናይትድ በሻምፒዮንስ ሊጉ 2 ጎል ከተቆጠረበት በኋላ ሲያሸንፍ ይህ ለ 3ተኛ ጊዜ ነው።
በዚሁ ምድብ ያንግ ቦይስ በሜዳው ቪላርያልን አስተናግዶ 3-1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።ጨዋታው አንደተጀመረ በ6 ደቂቃ ላይ ጎል ማስቆጠር የቻለው 19 አመቱ ዬርሚ ፒኖ በሻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ በልደቱ ቀን ጎል ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
ምድብ 7 የኦስትሪያው ሳልዝበርግ የጀርመኑን ዎልፍስበርግ በሜዳው ሬድ ቡል አሪና አስተናግዶ 3-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።ይህም የጀርመን ቡድን አስተናግዶ ያሸነፈ የመጀመሪያው የኦስትሪያ ቡድን ያደርገዋል። በዚሁ ምድብ ጨዋታቸውን ያካሄዱት ሊል እና ሲቭያ ያለግብ 0-0 አቻ ውጤት ተጠናቋል።
ምድብ 8 የምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ ስዊድን ሊግ የሚጫወተውን ማልሞ በሜዳው ስታም ፎርድ ብሪጅ አስተናግዶ 4-0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።በዚህ ጨዋታ
ተከላካዩ አንድሪያስ ክሪስተንሰን የመጀመሪያ ጎሉን ለሰማያዊዎቹ ማስቆጠር ችሏል። 137ጨዋታዎችን ለ ቼልሲ ማድረግ የቻለው ይህ ዴንማርካዊ እስከ ትላንት ምሽት ድረስ ለ ቼልሲ አንድም ግብ ማስቆጠር አልቻለም ነበር። ቀሪውን ግቦች በ 21 ኛው እና በ 57 ኛው ደቂቃ የተገኙትን የፍፁም ቅጣት ምቶች ጆርጊንሆ ወደ ጎል ሲቀይር ቀሪዋን 1 ጎል ካይ ሀቨርትዝ በስሙ አስመዝግቧል።
በዚሁ ምድብ ወደ ጋዝፕሮም አሪና አቅንቶ ዜኒትን ያገኘው የአሌግሪው ቡድን ጁቬንቱስ በ86 ደቂቃ የኩሉሴቭስኪ ጎል ታግዞ 1-0 አሸንፎ ተመልሷል።
ሚካኤል ደጀኔ
