ኢትዮ ቴሌኮም የ4ጂ የሕዝብ ቁጥር ሽፋን 82.23 በመቶ መድረሱ አስታወቀ!
የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በሰጡት ረጅም ማብራሪያና ገለጻ ላይ በበጀት ዓመቱ 215.82 ቢሊዮን ብር ገቢ በማመንጨት የዕቅዱን 99.7 በመቶ ማሳካቱን አስታውቀዋል።

እንዲሁም የኩባንያው ደንበኞች ቁጥር 90.12 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን የፋይናንስ አካታችነትን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ ድርሻ ያለው የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚዎች 60.6 ሚሊዮን መድረሱን በመግለጽ በተጨማሪም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ የታሪካዊ ስኬት ምዕራፍ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዳታና ኢንተርኔት አገልግሎት የተገኘው ገቢ 31.1 በመቶ ከሞባይል ድምፅ ገቢ 23.5 በመቶ ብልጫ በመውሰድ ኩባንያው ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ያደረገውን ስኬታማ ሽግግር በግልጽ ማሳየቱን አብራርተዋል።
ቴሌብር በተመለከተ በበጀት ዓመቱ ብቻ 4.19 ትሪሊዮን ብር የሚያንቀሳቅስ 2.61 ቢሊዮን ግብይቶችን ያስተናገደ ሲሆን ተቋሙ ከወትሮው የቴሌኮም ኦፕሬተርነት ወደ ሁለንተናዊ የቴክኖሎጂ ተቋም የመሸጋገር ጉዞውን በተሳካ ሁኔታ እያከናወነ መሆኑ እንዲሁም ሌሎች በርካታ የኩባንያው ስራዎች አፈጻጸም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በሰፊው ተብራርቷል።
በመጨረሻም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ሰፋ ያለምላሽ ሰጥተዋል።
✍️ ፈለቀ ደምሴ
