መኝታ የተከለከለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን
ዛምቢያ ንዶላ ያቀናው የኢትዮጵያ እትሌቲክስ ልዑካን ቡድን በመኝታ እጦት መሬት ላይ እንደተኙ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፌስቡክ ገፁ ቡድናችን መኝታ በማጣት እስከዚህ ሰአት ድረስ ማረፊያ አላገኘም፣ ከውድድሩ ስፍራ ከ65 ኪሜ በላይ ርቆ እንዲሄድም ተደርጓል። ሆኖም ከፈለጋችሁ መሬት ላይ ልትተኙ ትችላላችሁ ብለውናል። ሲሉ አክለው ፅፈዋል ።